ቻይናና ግብጽ በኢንዱስትሪና በኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ውይይት ሊያደርጉ ነው

ቻይና በግብፅ የኢንዱስትሪ ዞኖችን በመስፋፋትና የኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩ    ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት በግብፅ  እንደሚያካሄዱ ተገለጸ ፡፡

በሁለቱ አገራት የትራንስፖርት፣ የኢንዱስትሪና የኃይል  ምርት ፕሮጀክት አቅምን በማሳደግ ላይ ያተኮረ ሶስተኛው የግብፅ- ቻይና የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ በካይሮ ይካሄዳል፡፡

በሁለቱ አገራት በሚያደርጉት ወይይት የጋራ ኢንቨስትመንት ሁኔታን የሚዳስስ ሲሆን በውይይቱ የሃገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ጣሪቅ ካቢልና የቻይና ብሔራዊ ልማት ሪፎርም ኮሚሽን ምክትል ዳይሬክተር ኒንግ ጂዚህ ይገኙበታል፡፡

ቻይና እያካሄደች ያለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም እድገት፣ በተለይ ደግሞ በዓለም  ንግድ፣ በአየር ንብረት መሻሻል ላይ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን  የግብፅ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ  ካቢል ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ቻይና ከግብፅ ጋር በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ወቅቱ አመቺ መሆኑን  ተናግረዋል ፡፡

በተለይ በቻይና የሚመራውና ከ150 ቢሊየን ዶላር በላይ የተመደበለትና የተለያዩ አገራትን በሲልክ ሮድ ያገናኛል የተባለለት የዋን ቤልት ዋን ሮድ የትብብር ፕሮጀክት ግብፅን ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርጋታል ሲሉ ካቢል አክለው ተናግረዋል፡፡

የቻይና ብሔራዊ ልማት ሪፎርም ኮሚሽን ምክትል ዳይሬክተር ጃዚህ በበኩላቸው ግብፅ ከመካከለኛ ምስራቅና ከሰሜን አፍሪካ ከሚገኙ ሃገራት መካከል  ለቻይና የቅርብ ወዳጅ ሃገር ናት ብለዋል ፡፡

ቻይናን ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ለሚያገናኘው የትብብር ፕሮጀክቱ ላይ ግብጽ  መካተቷ የወደፊት የሁለቱ ሃገራት ወዳጅነትንም የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡

ቻይና ከምትገነባቸው 10 የኢንዱስትሪ ዞኖች መካከል አንዱ በምዕራባዊ የስዊዝ ባህረ ሰላጤ ክፍል ላይ ነው፡፡

ይህ ደግሞ ከሁሉም አካባቢዎች በበለጠ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጡ ምርቶቹን በቀላሉ ወደ ገበያ ለማቅረብና ወደ ተለያዩ ሃገሮች ለመላክ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ የንግድ ስምምነቱ ከግብጽና አለም አቀፍ በገበያ ከተጣመሩ አካላት ጋር የተፈፀመ ነው ሲሉ ጃዚህ የገለፁት፡፡

ካቢል በቤጂንግ የመኪና ማምረቻ፣ የጥሬ እቃ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፣ የስፖርት ጫማ ማምረቻ ኩባንያዎች ጎብኝተዋል ፡፡

ሃዋታይ ሞተርስ የተባለው ኩባንያ የመኪና ምርታቸው በቀላሉ በአፍሪካ ገበያ ላይ ለማድረስ በቀጣይ በግብፅ የመኪና እቃዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለመክፈት ፍላጎት እንዳለውና ለመዋዕለ ነዋዩ  ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት እንደተያዘ  የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ለ ካቢል ቃል ገብተውላቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ሃዋታይ ሞተርስ ሊገነባው ያሰበውን ፕሮጀክት መሳካት ያግዝ ዘንድ  ግብፅ በመምጣት ለፕሮጀክቱ አስፈላጊውን ጥናት መድረግ እንደሚችልና በስዊዝ ካናል የኢኮኖሚ ዞን ወይም ልላ የመረጡት ቦታ መጎብኘት እንደሚችሉም ጠቁመዋል። ( ምንጭ: ኢጅፕት ዴይሊ ኒውስ)