ፓን አፍሪካ ኢኮ ባንክ ስኬታማ በመሆን ሽልማት አገኘ

ፓን አፍሪካ ባንክ እኤአ በ2017 የዓለማችን ስኬታማ ባንክ በሚል በሁለት መስፈርቶች ሽልማት ማግኘቱ ተገለጸ ።   

በእንግሊዝ ለንደን በተዘጋጀው የ2017 ስኬታማ እና ትርፋማ ባንኮች ሽልማት በሁለት ዘርፎች በማሸነፍ ቀዳሚ ተሸላሚ ለመሆን ችሏል ነው የተባለው፡፡

ለዓለማቀፍ ባንኮች መመዘኛ ከወጡት መስፈርቶች መካከል በአዳዲስ ሀሳቦች እና ቴክኒኮች ፈጠራ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ደረጃን አስጠብቆ በመቆየት  በሚሉት ዓለማቀፍ መስፈርቶች ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የቁጠባ ባህል በማሳደግ የደንበኛ ቁጥር መጨመር ላይ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለሌሎች አርዓያ እንደሆነም ተጠቅሶ ምስጋና ተችሮታል፡፡

ኢኮ ባንክ በአፍሪካ ላሉ የግል እና የመንግስት ባንኮች  ተሞክሮ በማካፈል በአህጉሪቱ የፋይናንስ አቅም በመጨመር የድርሻውን እየተወጣ ያለ ተቋም  መሆኑን ነው የተገተለጸው ፡፡

ባንኩ ላቋቋሙት አገራትም ሆነ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እና አገራ ለመሰረተ ልማት እና ግዙፍ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበት በመሆኑ አላማውን ያሳካም ነው ተብሏል፡፡

ፓን አፍሪካ ባንክ ለደንበኞቹ እና ለራሱም የስኬት ምንጭ ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ የባንኩ መስራችና ባለቤቶች 36 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከ19 ሺ በላይ ሰራተኞች ከአርባ በላይ አገራት ባሉ 1200 ያህል ቅርንጫፎች እንደሚያስተዳር ተጠቁሟል ፡፡

ባንኩ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በአነስተኛ አምራችነት እና ስራ ፈጠራ ዙሪያ ለተሰማሩ ግለሰብ፣ ድርጅቶች እና አገራት  የገንዘብ ብድር አገልግሎት፣ የአዋጭነት ጥናት ድጋፍ እና  እርዳታ እንደሚያደርግ ነው የተመለከተው ፡፡

ባንኩ በቀጣይ አቅሙን በማሳደግ በተለያዩ አገራት ቅርንጫፎቹን በመክፈት እና ተደራሽነቱን በማስፋት አፍሪካውያንን ጥቅም ይበልጥ እንደሚሠራ አመልክቷል ።

አፍሪካ በፋይናንስ አቅሟ የምዕራባውያንን እጅ የማታይበት ለወደፊቱ እንደ አይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ተስፋ እንደሚሆን ባንኩ ገልጿል፡፡

አፍሪካውያን ለጋራ እድገታቸው እና ትብብር ሲሉ የዛሬ ሦስት አስርት ዓመታት ገደማ ያቋቋሙት የአፍካውያን ባንክ ነው ኢኮ ባንክ፡፡

በምጣኔ ሃብቷ እና እድገቷ ሦስተኛውን ዓለም ደረጃ ለዘመናት የያዘቸው አፍሪካ አሁን በህብረቷ  ለመጠናከር የሚያስችላትን የመሠረተ ልማት ዝርጋታም ሆነ ለሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ፈጥኖ እንዲደርስ  የገንዘብ ተቋሙ እኤአ በ1988 በቶጎ ሎሜ እንደተመሰረተ ለማወቅ ተችሏል ፡፡

 ( ምንጭ: ዴይሊ ኔሽን )