18 የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ አውሮፓ እንዳይበሩ ታገዱ

መሠረታቸው በአፍሪካ አህጉር የሆኑ 18 የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ አውሮፓ እንዳይበሩ መታገዳቸውን የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን አስታወቀ።

በአየር መንገዶቹ ላይ እገዳ የተጣለው የደህንነት ስጋትን ለመቆጣጣር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን  የታጠቁ በመሆናቸው ነው ተብሏል ።      

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ናይጄሪያን ጨምሮ የ18 ሀገሮች ወደ አውሮፓ እንዳይበሩ ያገደው አለም አቀፍ መሥፈርት የማያሟሉ በመሆናቸው ነው ።  

ህብረቱ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በአውሮፓ ምድር እንዲበሩ የማይፈቀድላቸው አየር መንገዶች  ዝርዝር ሲወጣ  የናይጄሪያ አየር መንገድ በቀዳሚነት ሥፍራ ላይ ትገኛለች ፡፡

የአውሮፓ ህበረት ኮሚሽን ባወጣው መረጃ መሠረት በፍፁም የተከለከሉ  የማስተናገጃ ሥርዓት ተከትለዋል ያላቸውን አየር መንገዶችን ሲያግድ በጉዳዩ ላይ በምንም መልኩ እንደማይደራደር በማሳወቅ ነው፡፡  

በእገዳው ውስጥ ተካተው ከነበሩት ሀገራት መስፈርቱን በማሟላታቸው ቤኒን እና ሞዛቢክ ከዝርዝሩ መፋቅ ችለዋል፡፡ 

የናጄሪያው አየር መንገድ ወደ አውሮፓ ሀገሮች በሳምንት አራት ቀን በቦይን 767  ቀጥታ በራራ ከ2015 ጀምሮ እያደረገ እንደነበር ይታወሳል ።