ታንዛንያ እና ኬንያ የንግድ ትስስር ማዕቀብ ለማንሳት ተስማሙ

ታንዛኒያና ኬንያ  በመካከላቸው የነበረውን የንግድ ትስስር ማዕቀብ ለማንሳት  ተስማሙ  ።

ኬንያ እና ታንዛኒያ ዲፕሎማሲያዊ ሆነ የንግድ ግንኙነት አቋርጠው ቆይተዋል፡፡

በኬንያ ናይሮቢ የታነዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ እና የኬንያው አቻቸው ኡሁሩ ኬንያታ ካደረጉት ውይይት በኋላ ነበር ታንዛንያ እና ኬንያ በመሃከላቸው የነበረውን የንግድ ትስስር ማዕቀብ ለማንሳት የተስማሙት፡፡

ውሳኔው ኬንያ ከታንዛኒያ የምታስገባቸውን  የዱቄት እና የጋዝ እገዳ የሚያነሳ ሲሆን በሌላ     በኩል ታንዛኒያ ከኬንያ  የምታስገባቸውን ወተት እና ሲጋራ በስፋት እንድታስገባ የሚያስችል   ይሆናል፡፡

 ኬንያ በታንዛንያ ላይ የጣለችው እገዳ በጥራት ምክንያት ቢሆንም ታንዛኒያም በመልሱ ወደ     ኬንያ የሚገቡ የመኪና ጎማዎች እና ወተት ላይ እገዳዋን አድርጋ ነበር፡፡ ታንዛንያ በተጨማሪ ከዛምቢያ ወደ ኬንያ የሚገባውን የበቆሎ ምርትም በእሷ ምድር እንዳያልፍ ከልክላ ነበር፡፡

የታንዛንያ የኢንዱስትሪ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጸሀፊ አዶልፍ ማኬንዳ እንዳሉት   በባለፈው ወር በሁለቱ ሀገራት መካከል ስምምነት ላይ እሰከተደረሰበት ጊዜ ድረስ ከናይሮቢ ምንም  አይነት የንግድም ሆነ የዴፕሎማስያዊ ግንኙነት አልነበረም፡፡

 ኬንያ የታንዛኒያን ነጋዴዎች ያለምንም አጥጋቢ ምክንያት ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ከልክላለች   የምትለው ታንዛንያ ከክልከላው በኋላ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ንፋስ እንደገባበት ታንዛንያ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሯ በኩል ትናገራለች።

 ባለፈው ወር መጨረሻም የታንዛኒያ አስመጪና ላኪዎች ወደ ናይሮቢ እንዳይገቡ  በመታገዱና የምግብ ማብሰያ ጋዝ እንኳን እንዳያልፍ በማገዷ ንዴት ተሰምቷቸው እንደነበረ አልደበቁም፡፡  

 በሁለቱም ሀገራ መካከል ተደርጎ የነበረው የዘይት እና የዱቄት እገዳ ከምስራቅ አፍሪካ   ማህበረሰብ የንግድ ህግ ጋር የሚቃረን እንደነበረ ፐሮፌሰር ማኬንዳ ገልጸዋል፡፡