ናይጀሪያ ከደረሰባት የምጣኔ ሀብት ድቀት ማገገም መቻሏን ገለፀች

ናይጄሪያ ከደረሰባት የምጣኔ ሃብት ድቀት ለማገገም መቻሏን ገለጸች።  

የናይጀሪያ ምጣኔ ሃብት ከደረሰበት ድቀት በማገገም በሁለተኛው እሩብ አመት የተሻለ እድገት ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡ የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ከአመት አመት ጭማሪ እያሳየ መምጣቱን ጠቅሶ ጭማሪው 0ነጥብ 55 በመቶ መሆኑን የሀገሪቱ የስታስቲክሰ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የናይጄሪያ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ምጣኔ ሃብቱ አሁንም ስጋት ላይ መሆኑን እና የበለጠ መሥራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በአፍሪካ ግዙፍ ምጣኔ ሃብት ያላት ናይጀሪያ በ25 አመታት ውስጥ ገጥሟት የማያቀው  የምጣኔ ሃብት ድቀት የገጠማት ሲሆን  እኤአ ከ2016 ጀምሮ ግን የተሻለ የሚባል እድገት እያስመዘገበች እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ለዚህም ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የምጣኔ ሃብት ድቀቱ 1ነጥብ 5 በመቶ መቀነሱ ነው የተነገረው፡፡

በተለይም እኤአ በ2017 የመጀመሪያው ሩብ አመት ላይ እንደነበር የተገለፀ ቢሆንም በነዳጅ ሽያጭ ላይ የተገኝው ገቢ ዝቅተኛ እንደሆነ እና የተገኝው የውጭ ምንዛሪም በተመሳሳይ ዝቅተኛ መሆኑ ምጣኔ ሃብቱ የተፈለገውን ያክል እንዳይሆን እንዳገደውም ተነግሯል፡፡ ቢሆንም በሁለተኛው እሩብ አመት ግን መሻሻልን አሳይቱል ብሏል ሮይተርሰ በዘገባው፡፡

ለዚህም እንደ ምክንያት ከቀረቡ ነገሮች ውስጥ ባለፈው አመት በሀገሪቷ የሚገኝ ነዳጅ ማከማቻዎች ላይ የተፈፀመ ጥቃት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ይህም የተፈለገውን ያክል የነዳጅ መጠን ማግኝት እና ለሸያጫ ማቅረብ እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

በሁለተኛው እሩብ አመት ግን 1ነጥብ 84 ሚሊየን በርሚል ነዳጅ በቀን ማግኝት መቻሉን የተገልፀ ሲሆን ከዚህም የተሻለ ገቢ መገኝቱ ተጠቁሟል፡፡

ቢሆንም ግን በዘርፉ የተገኝውን ሰኬት ያክል የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳልቻለ ተገልፆ ምጣኔ ሀብቱን ጠንካራ ለማድረግ እና ወደፊት ለማራመድ የተሸለ መሰራት እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሁለተኛው ሩብ አመት ላይ የተገኝውን ሰኬት ማስቀጠል ከተቻለ የሀገሪቱን አመታው የገቢ መጠን አሁን ካለበት የተሻለ ማድረግ እንደሚቻልም የአፍሪካ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ የሆኑት ራዚያ ካን ተናግረዋል፡፡