ኢጋድ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረቱን እንደሚቀጥል አስታወቀ

በደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የተፈረመውን ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል  አስታውቋል ፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የኢጋድ አባል አገራት ቀደም ብለው ከተለያዩ ወገኖች ጋር  የጀመሩትን ምክክር ለመቀጠል በዛሬው ዕለት  ወደ ጁባ ያመራሉ ፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና የሱዳን፣ የኬንያ፣ የዮጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የጅቡቲና ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች በጁባ   በሚካሄደው   ምክክር  ላይ ይሳተፋሉ  ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

ባለስልጣናቱም ከደቡብ ሱዳን መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የተቃዋሚ ወገን መሪዎች ጋር ለመነጋጋር   ቀጠሮ  ተይዞላቸዋል ፡፡  

የኢጋድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀደሞ ሲልም ወደ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ከቀድሞ የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሬክ ማቻር ጋር መነጋገራቸው ይታወቃል፡፡