የሶማሊያው ፕሬዚደንት በአልሻባብ ላይ የበቀል እርምጃ እንደሚወስዱ አስታወቁ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ሙሀመድ ፋርማጆ በአልሸባብ ላይ የበቀል እርምጃ  እንደሚወስዱ ገለጹ ፡፡

የሶማሊያ ዋንኛው የሰላም ጠንቅ አል-ሸባብ ባለፈው ቅዳሜ ቁጥራቸው 300 ለሚሆኑ ንፁሀን ሞት ተጠያቂ ሆኗል፡፡

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ጥቃት ያስመረራቸው የሶማሊያ ዜጎች በመዲናቸው ሞቃዲሾ አውራ ጎዳና  ከእንግዲህ ደማችን በከንቱ መፍሰሱ ይብቃ ሲሉ ጠንካራ መልዕክታቸውን በሰላማዊ ስልፍ ገልፀዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ለሽብር ቡደኑ አል ሸባብ ያላቸውን ጥላቻም አንጸባርቀዋል፡፡ አልሸባብ በቅዳሜው የሽብር ጥቃት 300 የሚሆኑ ዜጎችን ገድሏል፡፡ ቱርክ ደግሞ ቁሰለኞችን አንካራ ድረስ ወስዳ እንዲታከሙ አድርጋለች፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መኪና ላይ በተጠመደ ቦንብ ህይወታቸውን ላጡ ወንድም እህቶቻቸው ቤተሰቦች የአብረናችሁ ነን የማጽናኛ ድምጻቸውን አንድ ላይ አሰምተዋቸዋል፡፡ 

የሶማሊያ ወጣቶች ነብሳቸውን እየቀማ ላለው አልሸባብ መክሰም ክንዳቸው እንደማይዝል ተናግረዋል፡፡ ቡድኑን ለማጥፋት እንደሚፋለሙም ገልጸዋል፡፡ 

በአስር ሺዎች በሚቆጠሩት የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ፊት የተገኙት  ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ሙሀመድ ፋርማጆ ከጥቃቱ ጀርባ ያሉትን በሙሉ መንግስት ይበቀላቸዋል ብለዋል፡፡

የአልቃይዳ የምስራቅ አፍሪካው ክንፍ  አልሸባብን ከሶማሊያ ለማስወጣት ሱማሊያውያን አንድ መሆን ይገባናል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱ የቀጠለው አልሸባብን ለመፋለም አንድነት ትልቁ መሳሪያ ቢሆንም ልዩ ሀይል ተቋቁሞ አልሸባብን ከመሸገበት አውጥቶ ራቁቱን ያስቀረዋል ሲሉ ዝተዋል፡፡Top of Form

Bottom of Form

Top of Form

Bottom of Form

በመዲናዋ ሞቃዲሾ የተካሄደው በአስር ሺዎች የታጀበው የፀረ አል ሸባብ ሰላማዊ ሰልፍ በፑንት ላንድ፤ጁባላንድ፤ጋልሙዱግ ክልሎችም ተደግሟል፡፡

የሀገሪቱ መንግስት ፖሊስ ከሽብር ጥቃቱ ጋር ተያይዞ በርካቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ቢገልጽም ያዝኩኝ ከማለት ያለፈ ጠለቅ ያለ መረጃ ግን አልሰጠም፡፡

እስካሁንም ደማቸው በከንቱ ለፈሰሰው የሶማሊያ ዜጎች ሀላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም አለም ይህ እኩይ ተግባር የአል ሸባብ እንጂ የማን ሊሆን ይችላል እያለ ነው፡፡

የሶማሊያ መከላከያ አል  ሸባብን ለመዋጋት እያደረገ ባለው ጥረት የአፍሪካ ህብረት 22 ሺህ ሰላም አስከባሪ እያገዘው ይገኛል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሳህል ሀይል በሚል ስያሜ ከአምስት አፍሪካ ሀገራት ጋር የሰላም ማስከበርና የጸረ ሽብር ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛል፡፡ ሱማሊያ ለደረሰባት ዱብ እዳ እነ ጁቡቲ፤ኬንያ፤አሜሪካና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምላሽ ለመስጠት ቢጥሩም ሶማሊያ ያስደሰታት የቱርክ ምላሽ ነው፡፡

የሞቃዲሾ ከንቲባ በቲውተር ገጻቸው ላይ ቱርክ ለምላሷ ታላቅ ምስጋና ይገባታል ብለዋል፡፡ ከጉዳታችን እንድናገግም አድርጎናል ሲሉ በቲውተር ገጻቸው  አስፍረዋል፡፡

አንካራ ባለፉት አምስት አመታት በሶማሊያ ትርጉም ያለው ኢንቨስትመንት አካሂዳለች፡፡ዋና ምክንያቷ ደግሞ ሶማሊያ በኢኮኖሚ ብትጠነክር ምናልባት ሰላሟ ሊመለስ ይችል ይሆናል በሚል ነው፡፡

እንደ ሀገር ለመቆም የተቸገረችው ሶማሊያ ካስተናገደችው የሽብር ጥቃት ሁሉ ቅዳሜ ዕለት  ፈንጅ ጭኖ በጋለበባቸው አሸባሪ የሞቱትና የቆሰሉት ዜጎቿ በታሪኳ አይታው የማታቀው ስለመሆኑ የአለም ብዙኋን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡