በኬንያ ለምርጫ ከተመዘገቡት 34 በመቶ የሚሆኑት ብቻ መምረጣቸው ተገለጸ

በኬንያ ዳግመኛ በተካሄደው  ምርጫ የተሳተፉ መራጮች ከተመዘገቡት ከ34 በመቶ እንደማይበልጡ የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡በዚህም ከነሐሴው ምርጫ የተሳታፊዎች ቁጥር እጅግ ቅናሽ ማሳየቱ ነው የተመለከተው፡፡

በመጀመሪያው ምርጫ ከተመዘገቡት 80 በመቶዎቹ ድምጽ ሰጥተው እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተቀዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቻቸው በምርጫው እንዳይሳተፉ ጫና ማሳደራቸው ተፅዕኖ ማሳደሩን ቢቢሲ በዘገባው አትቷል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር በፈጠሩት ግጭት በአራት አካባቢዎች ምርጫው ሳይደረግ ቀርቷል፡፡

ረብሻ በተነሳባቸው አካባቢዎች የተቋረጠው ምርጫ ቅዳሜ እንዲካሄድ መወሰኑን  የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኦዲንጋ ከምርጫው ራሳቸውን ቢያገሉም ፕሬዝዳንት ኬንያታ በሁለተኛው ምርጫም ተሳትፈዋል፡፡ በግጭቱም ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡