ሩስያ በናይጄሪያ የኒውክለር ማብላያዎችን ልትገነባ ነው

ሩሲያ በናይጄሪያ  ሁለት ግዙፍ ማብላያዎችን ለመገንባት የሁለትዮሽ  ስምምነት ማድረጋቸው ተገለጸ ፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትልቁ የናይጄሪያ ኢኮኖሚ እያጋጠመው ያለውን የሀይል እጥረት ይቀርፋሉ የተባሉት  ፕሮጀክቶች   በሀገሪቱ ደቡባዊና ማዕከላዊ ስፍራዎች ላይ እንደሚገነቡ የናይጄሪያ አቶሚክ ሀይል ኮሚሽን ለቢቢሲ ገልጿል፡፡

ትክክለኛው የፕሮጀክቶቹ  ወጭ ባይታወቅም እስከ 20 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚገመት  የሀገሪቱ ብዙኋን መገኛዎች ዘግበዋል፡፡ ግንባታውን የሚያካሂደው የሩስያ ድርጅት ከ ደቡብ አፍሪካና ጋና ጋርም ድርድር ስለመጀመሩ ታውቋል፡፡

ከናይጄሪያ ጋር የተደረገው ስምምነት ድርድሩ የተጀመረው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 2009 ላይ ነው ፡፡

ይህ ረጅም ግዜ የፈጀው የሁለቱ ሀገራት ድርድር ከዳር የደረሰው ሁለቱ ሀገራት በኒውክለር ፕሮግራም አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ማብላያዎቹ በቀጣይ ሁለት አመታት ግንባታቸው ይካሄዳል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡