ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ትናንት በፍቃዳቸው ከሥልጣን ለቀቁ ።
የፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ከሥልጣን መልቀቅን ተከትሎም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዚምባቤያውያን ትናንት ምሽት ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል ።
አንድ ዚምባብያዊ እንደገለጸው ሙጋቤ ለ37 ዓመት በሥልጣን ቆይቷል እግዚአብሔር ብቻ ነው አሱን ማንሳት የሚችለው ብሏል ።
አንዳንድ አፍሪካውያን ሮበርት ሙጋቤ የአፍሪካ ነጻነት ጀግና መሆኑን እየገለጹ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሙጋቤ አምባገነን መሪና የዚምባብዌን ኢኮኖሚ ከጥቅም ውጭ ያደረገ መሆኑን ይናገራሉ ።
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የዚምባብዌ ፓርላማ ስብሰባ ላይ የፓርላማው አፈጉባኤ ከሮበርት ሙጋቤ የተጻፈውን የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ በፓርላማው ተነቧል ።
ሙጋቤ በጻፉት የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ላይ እንደገለጹት ከህዝቡ በመጣው ግፊት ፣ የዚምባብዌ ሠራዊትና የገዥው ፓርቲ ባሳደሩት ጫና ምክንያትና በአገሪቱ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማስቻል በፍቃደኝነት ከሥልጣናቸው መልቀቃቸው አስታውቀዋል ሙጋቤ ።
የዚምባብዌ ገዥ ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍ የህግ አውጪ የሆኑና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በዚምባብዌ መልቀቅ የተሰማቸው የደስታ ስሜት በፓርላማው የገለጹ ሲሆን ዚምባብያውያን በሙጋቤ መልቀቅ ምክንያት በየመንገዱ የዳንስ ፣ የዘፈን ፣ የፈንጠዝያ ጭፈራቸውን ትናንት ምሽት ሲያሳዩ ታይተዋል ።
ጁሊያን ምቱኩዲዚ ለኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገረው በሙጋቤ ከሥልጣን መልቀቅ እጅግ መደሰቱንና ይህ ወቅት ለዚምባብዌ እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል ።
እስካሁን በዚምባብዌ እየተፈጠረ ባለው ሁኔታ እንቅልፍ አጥተን ቆይተናል ያለው ምቱኩዲዚ አሁን ፍላጎታችብ በመሳካቱ ደስታው የላቀ መሆኑብ ለቢቢሲም አክሎ ገልጿል ።(ምንጭ : ቢቢሲ)