በሶማሊያ በጁባ ላንድ በሁለት ቀናት 26 ሰዎች በረሃብ መሞታቸው ተጠቆመ

በድርቅ በተመታችዉ በሶማሊያ ከፊል ራስ-ገዝ መስተዳድር ጁባ ላንድ ዉስጥ 26 ሰዎች በረሃብ መሞታቸው ተመለከተ ።

ሮይተር ዜና አገልግሎት የመስተዳድሩን ራዲዮ ጣቢያ ጠቅሶ እንደዘገበዉ፤ሰዎች የሞቱት ከፍተኛ የምግብ እጥረት በተከሰተባቸዉ ጁባ እና ጌዶ በተባሉት ከተሞች መካካል በሚገኙ አነስተኛ ከተሞች ነዉ።

በዘገባዉ መሠረት 26ቱም ሰዎች የሞቱት ባለፈዉ እሁድ መጋቢት 10 እና 11/2009 ዓም መሆኑን አስታውቋል ።

ዓመታት የዘለቀዉ የሶማሊያ ጦርነት፤ከድርቅ ጋር ተዳምሮ የሐገሪቱን ሕዝብ በየጊዜዉ ያስርባል፤ያሰድዳል ይገድላልም ነው ያለው ።

ዘንድሮም በርካታ ሕዝብ ለምግብ ዕጥረት ከተጋለጠባቸዉ ሰዎት የአፍሪቃ ሃገራት ሶማሊያ አንዷ ናት።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለዉ ሶማሊያ ዉስጥ ከ6ነጥብ2 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ያስፈልገዋል።

በቂ ርዳታ ፈጥኖ ባለመድረሱ አቅመ ደካሞች፤ ሕፃናትና ከብቶች እየሞቱ መሆኑን ዶች ዌለ ዘግቧል ።