ናይጄሪያ ለማህበራዊ ደህንነት የሚውል 2 ቢሊዮን ዶላር ልትመድብ ነው

ናይጀሪያ ለሃገሪቱ ማህበራዊ ደህንነት መረሃ ግብር የሚውል 2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ እንደምትመድብ አስታውቃለች፡፡

ከምትመድበው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ከዓለም ባንክ በሚገኝ ብድር ይሸፈናል ተብሏል ፡፡

በአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚ የሆነችው ናይጀሪያ ባለፉት ዓመታት በተከሰተው የአሸባሪዎች ጥቃት በምጣኔ ሃብቷ ላይ በፈጠረው አለመረጋጋት በርካቶች ለድህነት ተዳርገዋል፡፡

የብሉምበርግ ዘገባ እንደሚያሳየው ከሆነ በኑሮ የተጎዱ የሃገሪቱ ዜጎች  ልጆቻቸውን ማስተማር እንዳልቻሉና የስራ አጥነት ቁጥሩም እየጨመረ ይገኛል፡፡

የሃገሪቱ  ማህበራዊ ደህንነት መርሃ ግብርም የናይጀሪያን የምጣኔ ሃብት ቀውስ ለመቅረፍ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ እንደሚመድብ አስታውቋል፡፡

ከሚመደበው 2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ግማሽ ቢሊዮን ዶላሩ ከዓለም ባንክ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ይሸፈናል ተብሏል፡፡

ገንዘቡ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታትና የተሻለ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲኖር በማድረግ ምጣኔ ሃብቷን ያሳድገዋል ነው የተባለው ፡፡

የሃገሪቱ የመንግስት በጀትና ብሔራዊ እቅድ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ዘይነብ አህመድ መረሃ ግብሩ ሲጀመር ከ36ቱ የናይጀሪያ ግዛቶች ውስጥ በስምንቱ ላይ የሚተገበር  ሲሆን 1ሚልየን አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል ፡፡

በዚህም የተሸለ የገንዘብ ዝውውር እንዲኖርና ዜጎችም የተለያዩ የፋብሪካ ምርቶችን እንዲጠቀሙ በማድረግ አምራቾች በዛ ያለ የስራ ዕድል በመፍጠር የሃገሪቷን ምጣኔ ሃብት ያሳድገዋል ብለዋል፡፡