ኡጋንዳ ለመንግሥት ሠራተኞች የአለባበስ ደንብ አወጣች

ኡጋንዳ በሁሉም  የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች  ተግባራዊ የሚሆን  የአለባበስ ደንብ አወጣች ።  

የዮጋንዳ መንግሰት ለሁሉም የሚኒሰትር መሰሪያ ቤቶች  ጥብቅ ማሳሰቢያ አሰተላልፏል፡፡ መመሪያው ማንኛውም የመንግሰት ሰራተኛ የፈለገውን ልብሰ ለብሶ ስራው ቦታ ላይ አይችልም፡፡

መንግሰት ባወጣው የአለባበሰ ሰርአት መሰረት የአለበበስ ስርዓት ውስጥ ሆኖ ስራውን ማከናወን  እንዳለበት የወጣው ህገ  ደንብ ደንግጓል፡፡

ህጉ የመንግሥት ሰራተኞች በተለይ ደግሞ ሴቶች አለባበሰቸው ቅጥ ያጣ የሚባል ደረጃ መድረሱን አንሰተው ይህንን ለማሰተካከል እና ሰርአቱን የጠበቀ አለባበሰ በሰራ ገበታ ላይ መለበሰ እንዳለበትም አሳውቀዋል፡፡

ሴቶች ከጉልበታችው በላይ የሆነ ቀሚስ ፣ተረከዝ ያለው ጫማ ፣ ሰውነትን የሚያጣብቅ ማንኛውም ልብስ  ፣ ደማቅ ቀለም ያላቸው ልበሶች እንዲሁም ወንዶችን ለወሲብ የሚጋብዝ ማንኛውም አይነት አለባበሰን የኡጋንዳ መንግስት ከልክሏል፡

ከዚህም በተጨማሪ ደማቅ ቀለም ያላቸው የጥፍር ቀለሞች፣  ጥፍርን ማሰረዘም ፣ ቀለም ያላቸው ረጃጅም አርቲፊሻል ፀጉሮች  መጠቀም እንደማይችሉ እና ፊታቸውንም የተጋነነ ሚካፕ እንዳይጠቀሙ  ደንቡ ያዛል፡፡  

ማንኛውም  ሴት ሠራተኛ ዘርፈፍ ያለ ቀሚሰ ደልደል ያለ ጫማ በማድረግ  ብቻ የመንግሥት ሥራ መሰራት ያለበት ብለዋል፡፡

ታዲያ ይህ ህግ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም ያጠቃልላል ነው የተባለው፡፡ ወንዶችም ቢሆኑ የተጣበቀ ሱሪ ፣ ከጉልበት በላይ የሆነ ቁምጣ ፣ ወትሮ ከሚለበሰው የሽሚዝ አይነት ውጭ እንዳይነብሱ  ተደንግጓል፡፡

የሀገሪቷ የፕብሊሰ ሰርቪሰ ሚኒሰትር የሆኑት ሚኒሰትር ካትሪን ባራትታ ዋት ሙንቪዬር በሰጡት ጋዚጣዊ መግለጫ ሁሉም የዩጋንዳ ባለሰልጣናትና የሚመለከታቸው የሰራ ሀላፊዎች ህጉ በህብረተሰቡ እና በመንግሰት ሰራተኛው ዘንድ በአግባቡ እንዲተገበር እና ተቀባነት እንዲኖረው ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው እና ሰራተኞችም በወጣው የአለባበሰ ሰርአት መሰረት መሆን እንዳለበት አሳሰበዋል፡፡

ሀላፊዎቹ እንደሚሉት ከሆነ ይህንን ህግ ለማውጣት የተገደድነው ሰርአት የሊለው አለባበሰ በመበራከቱ ተገልጋዮች ወዳላሰፈላጊ ድርጊት እንዲገቡ ይጋብዛል ይህ ደግሞ ሀገርንም ግለሰብንም የሚጎዳ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለወሲብ የሚጋለጡ ዜጎች ቁጥር በመበራከቱ እና አሳሳቢ ደረጃ በመድረሱ ይህንን ህግ ለማውታት ተገደናል በለዋለል፡፡

ህጉን የማይተገብር ማንኛውም የመንግሰት ሰራተኛ ያለምንም ማሰጠንቀቂያ እርምጃ እንደሚወሰድበትም ነው የተገለፀው፡፡

አገልጋዮንም ተገልጋዩንም የማያሳቅቅ አለባበሰ መልበሰ በተለይ ለሰራ ገበታ ሁነኛ መፍትሄ ነው ተብሏል ፡፡