ደቡብ ሱዳን የጊኒ ዋርም በሽታን በማጥፋት ስኬታማ ተግባር እያከነወነች መሆኑ ተገለጸ

ደቡብ ሱዳን የጊኒ ወርም በሽታን ለማጥፋት ስኬታማ ተግባር እያከናወነች መሆኑ ተገለጸ ።  

በጦርነት ውስጥ ያለችው ደቡብ ሱዳን  የጊኒ ዋርምን በማጥፋት "ለሌሎችም ምሳሌ ሊያደርጓት ይገባል" ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር ተናገሩ ።

ጂሚ ካርተር የደቡብ ሱዳንን የጊኒ ወርምን ዘመቻ በማስመልከት አዲሲቷ ሃገር ካሉባት በርካታ ችግሮች አንፃር የጊኒ ዋርም በሽታን ለማጥፋት የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

በሽታው በተበከለ የመጠጥ ውሃ የሚተላለፍ ሲሆን በአብዛኛው በበሽታ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራትንም ሲጎዳ ይስተዋላል፡፡  

እኤአ በ2006 የጊኒ ዋርምን መከላከል ዘመቻ በይፋ በተጀመረበትበት ወቅት 20 ሺህ 500 ተጠቂዎች በሶስት ሺህ የገጠር ቀበሌዎች ተከስቶ ነበር፡፡ በወቅቱም ደቡብ ሱዳን በበሽታዉ ተጠቂ ከነበሩት ዘጠኝ ሃገራት ተርታ ተቀምጣ ነበር ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ሰዓትም በሽታውን ለማጥፋት ከሚጥሩት ቻድ እና ኢትዮዸያ ተርታ ተሰልፋለች፡፡

ዘንድሮ ደግሞ  የበሽታዉ ክስተት አለመኖሩን ሃገሪቱ ሪፖርት ያደረገች ሲሆን  ሃገሪቱ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለች በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከጊኒ ዋርም የፀዳች ሀገር ትሆናለች፡፡

አፈፃፀሙ አዲሲቷ ሀገር ካስመዘገበቻቸው ጥቂት ስኬቶች መካከል የሚጠቀስ ሲሆን ከአራት ዓመታት እርስ በርስ ጦርነት፡ረሃብ እና አሰቃቂ ሰብአዊ መብት አያያዝ ብሎም ከፍተኛ ወንጀል  ህዝቦቿን ለመታደግ እየጣረች ነው፡፡

ካርተር የጊኒ ዋርምን ከዓለም ለማጥፋት ከ30 አመታት በላይ ዘመቻ አድርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ 1986 በአመት ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሰዎች በአፍሪካ እና ኤሲያ ሃጉራት ባሉ 21 ሃገራት በበሽታዉ ይጠቁ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ክስተቱ ቀንሶ አሥር ደርሷል፡፡ይህ ውጤት የተመዘገበዉ በቻድ ነዉ፡፡

በመድሓኒትና በክትባት መቆጣጠር እንደሚቻለዉ በሽታ ሁሉ የጊኒ ዋርምም ህብረተሰቡ ንፁህ የመጠጥ ውሃን እንዲጠቀም በማስተማር መስቀረት ይቻላል፡፡

ቀጭን መሳዩ የጊኒ ወርም  ካበድ ህመምና ምልክት ሳያሳይ በሰዉነት ዉስጥ ለአንድ አመት መቆየት የሚችል ሲሆን በአብዛኛዉ  ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የሰዉነት ክፍሎችን ያጠቃል፡፡( ምንጭ: አሶሾየትድ ፕሬስ)