ለአፍሪካ የጤና አገልገሎት የሚሠጠው ድጋፍ መቀነሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

ለአፍሪካ ጤና አገልግሎት ማስፋፊያ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚደረገው ድጋፍ እየቀነሰ መምጣቱ ችግር እየፈጠረ  እንዳለ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

በአህጉሪቱ ያለው የሰላም እጦት ደግሞ ለህክምና አገልግሎት ያለው ፍላጎት በተቃራኒው እንዲጨምር አድርጓል፡፡

ባለፈው አንድ አመት ብቻ 216 ሚሊየን ሰዎች በዓለም ዙሪያ በወባ በሽታ ተይዘዋል፡፡ 90 በመቶ የሚሆኑት ታማሚዎች ደግሞ አፍሪካዊያን ስለመሆናቸው ከአለም ጤና ድርጅት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

አፍሪካ እ.ኤ.አ በ2013 የገጠማት የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ እንኳን 11ሺህ 300 አፍሪካውያን ሲሞቱ 28, 600ዎቹ ደግሞ የምዕራብ አፍሪካን ባጠቃው በሽታ በጊኒ፣ ሴራሊዮን እና ላይቤሪያ ከሞት ተርፈዋል፡፡

አልጀዚራ ከአለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማቲሺዲሶ ሞኢቲ ጋር በነበረው ቆይታ ስለ አፍሪካ የጤና አገልግሎት እና ተድግዳሮት አውግቷል፡፡

 በዚህ ወቅት አህጉሪቷ ከኢቦላ ቀውስ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ በገባችበት ጊዜ ምን ትምህርት ተገኘ አፍሪካን ከድጎማ ለማውጣት ምን መደረግ አለበት እና መሰል ጥያቄዎችን በማንሳት ማብራሪያ ጠይቋል፡፡

ዳይሬክተሯ ዶክተር ማቲሺዲሶ ሞኢቲ 47 በሚሆኑ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚታየው ድህነት የጤና ተቋማቶችን ለማዘመን የሚገጥመው ችግር የሃብት ውስንነት ትልቁ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡   

በዋናነት ከውጭ በሚገኝ እርዳታ ላይ የጤና አገልግሎታቸውን ጥገኛ ያደረጉ ናቸው ሲሉ ዳይሬክተሯ የአለም ጤና ድርጅት ለጤና ተቋማቱ የሚሠጠው እርዳታ በለጋሾች እጥረት ችግር እየገጠመው ስለመሆኑም አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የድርጅቱ ዳይሬክተር ሆኖ መመረጥ ለአፍሪካ ምን ጥቅም እያስገኘ እንደሆነ ለተነሳላቸው ሁለተኛ ጥያቄ መጠነ ሰፊ ጥቅም እያሰገኘ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ዶክተር ቴዎድሮስ ያላቸውን ክህሎት እና ልምድ በመጠቀም ዓለምን እንዲሁም አፍሪካን በተለየ መረዳት እንዲችሉ ማድረጉ ለስራቸው ውጤታማነት እያገዘ ነው ብለዋል፡፡

በአፍሪካ በገዳይነታቸው ከሚታወቁ በሽታዎች ውስጥ ወባ የሳንባ በሽታ እና ኤች አይቪ/ኤድስ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህን በሽታዎች ከአህጉሪቱ ለማጥፋት ስለሚሰራው ተግባርና የአለም ጤና ድርጅት እንቅስቃሴም በለመከተ  ማብራሪያ ተሠጥቷል ።

 የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማቲሺዲሶ ሞኢቲ በምላሻቸው ሰፊ ዘመቻ እየተካሄ ስለመሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል ብለዋል፡፡ ለበርካታ አስርት ዓመታት እየተሰራ ባለው ስራ ለውጥ እየታየ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ለውጡ ግን አጥጋቢ ሊሆን አልቻለም ያሉት ዳይሬክተሯ በተለይም የለጋሽ ሀገራት ድጋፍ መጠንከር እንደምክንያት አስቀምጠዋል፡፡

ወደፊት ድርጅቱ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የፋይናንስ ምንጭ በቋሚነት ማግኘት እንዲችል የአለም ጤና ድርጅት ከአጋር አካላት ጋር የቆየ ወዳጅነቱን በአዲስ ፖሊሲ ለመቀየር እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ 

ኢቦላን በመከላከል ሂደት የአለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ላይ ውድቀት አጋጥሞታል በሚል አልጀዚራ ወቀሳ አዘል  ጥያቄ  ለዳይሬክተሯ ያነሳው አልጀዚራ   በክስተቱ ሰፊ ትምህርት አግኝተናል ከማለት በተጨማሪ የበታሽው መጠን እና የአለም ጤና ድርጅት የሰጠው ግምት  መመጣጠን አለመቻላቸው በሽታው ከአቅም በላይ እንዲሆን ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ 

በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ገጠራማ ሥፍራዎች ያለው የጤና ተቋማት አቅም ውስንነትም ለውድቀቱ  አስተዋጽኦ  እንደነበረውም ሊዘነጋ እንደማይገባ  አስታውቀዋል፡፡