አንጎላ ያመጠቀችው ሳተላይት በመገናኛ ዘርፍ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋት ተገለጸ

አንጎላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጠቀችዉ ሳተላይት በመገናኛ ዘርፍ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋት እየተገመተ ነዉ፡፡

አንግሎ ሳት አንድ የተሰኘው የኮሙኒኬሽን ሳተላይት በራሽያ አጋርነት ወደ ትግበራ መግባቱ ታዉቋል ።

እኤአ  በ1975 ከፖርቹጋል ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣችዉ አንጎላ ከነጻነት ማግስት ካጋጣማት  በርካታ  ችግሮች  ተላቃ አሁን አዲስ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ለማምጠቅ መብቃቷ  ብዙዎችን እያስደነቀ  ይገኛል ።

በቅርቡ አልጄሪያ ከቻይና ጋር በመተባበር ተመሳሳይ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ማምጠቋ ዜና በተሰማ በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ አንጎላም ከራሽያ ጋር በመተባበር የቴክኖሎጂው ባለቤት ለመሆን በቅታለች፡፡ ሁለቱ ሀገራት በትብብር ያመጠቁት ሳተላይት ሰራዉን ጀምሯል ነዉ የተባለዉ፡፡

ሳተላይቱን የማምጠቅ ውጥን አንድ ብሎ የጀመረዉ እ.አ.አ በ2009 ሲሆን 300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መፍጀቱን የአንጎላ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል፡፡የአንግሎ ሳት አንድ የቆይታ እድሜ 15 አመት ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት ሳተላይቱን የመቆጣጠር ኃላፊነት የሀገሪቱ እንደሚሆን ታዉቋል፡፡

በብዛት የኩሙኒኬሽን ሳተላይት ሰሙ እንደሚያመለክተዉ ለመገናኛ ዘርፍ የሚዉል መሆኑን ተከትሎ አንግሎ ሳት አንድም ከተንቀሳቃሽ ስልክ ግንኙነት አገልግሎት ባለፈ ትልቅ ትርጉም እንዳለዉ ባለስልጣናቱ ይናገራሉ፡፡

የአንጎላ ቴሌኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ካርቫሎ ዳሮቻ የመገናኛ አገልግሎት አዉታርን ከማዘመን አልፎ በገጠራማ አካባቢዎች ከሆስፒታል ርቀዉ ለሚገኙ ዜጎች ለሚሰጠዉ የቴሌ ሜዲሲን አገልግሎትን እንደሚያዘምን ተናግረዋል፡፡

ናይጄሪያ፤ ጋናና ደቡብ አፍሪካ በህዋ ንፍቀ ክበብ ዉስጥ በርካታ ሳተላይት ያላቸዉ ሀገራት ናቸዉ፡፡አንጎላም እየተጠናቀቀ ባለዉ አመት የስፔስ ሳይንስ ዘርፍ እንዲዘመምን ባቀደቸዉ መሰረት ወደ ተግባር መግባቷን አሳይታለች፡፡ 

24 ሚሊዮን ዜጎች ያሏትና በአፍሪካ ቀዳሚ የነዳጅ አምራች ሀገራት ተርታ የምትሰለፈዉ አንጎላ በ1979 ወደ ሥልጣን የመጡትን ጆሴ ኤዲዋርዶ ዶስሳንቶስን የተኩት ጆኦ ሎሬንኮ ሀገሪቱ እንድትለወጥ ባደረጉት ጥረት አድናቆት እየተቸራቸዉ ነዉ፡፡

ናይጄሪያ ባመጠቀችዉ ሳተላይት አማካይነት ሽብርተኛ ቡድን የሆነዉን ቦኮ ሃራምን ለመቆጣጠር ስታውል፥ ሌሎች ሀገራትም ለሳይንስ ምርምር እያዋሉት ይገኛሉ፡፡ እኤአ በ2030 ናይጄርያ ለመጀመርያ ጊዜ የስነ ፈለግ ተመራማሪዎቿን ወደ ህዋ ለመላክ ግብ አስቀምጣለች፡

በአሁኑ ሰዓት በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሳተላይት ለማምጠቅ ዕቅድ ይዘዋል ፡፡ ኢትዮጵያና ኬንያም በ2016 ለአፍሪካ ህብረት የስፔስ ፖሊሲና ስትራቴጂ ዘርፍ እቅዳቸዉን በይፋ ማቅረባቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡( ምንጭ: አልጀዚራ)