በደቡብ ሱዳን የተራድኦ ደርጅቶች የምግብ አጥረቱን ለመከላከል ዝግጅት እያደረጉ ነው

በደቡብ ሱዳን ግጭት እና ድርቅ ያባባሱት የምግብ እጥረት የእርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር ቢያበዛውም የተራድኦ ደርጅቶች በአገሪቱ የተከሰተውን ረሀብ መቋቋም የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ግንቦት ድረስ የእርዳታ ድርጅቶች ለደቡብ ሱዳናዊያን እጃቸውን የማይዘረጉ ከሆነ የአገሪቱ ሶስት እጅ ህዝብ ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋላጭ ይሆናል፡፡

በደቡብ ሱዳን 7 ሚሊየን ዜጎች በአገሪቱ እንዲህ ለከፋ የምግብ እጥረት ሲጋለጡ ለመጀመሪያው ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

አገሪቱ ከተራድኦ ድርጅቶች እያገኘች ያለችው እርዳታ አነስተኛ መሆን ለምግብ እርዳታ ፈላጊዎቹ ቁጥር መበራከት ምክንያት ተብለው ከተጠቀሱት ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡

አሁን በዚህ ወቅት ግማሽ ያህል የአገሪቱ ህዝብ በየቀኑ በቂ ምግብ ማግኘት ያዳገተው ነው እንደ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች፡፡ አምና ከነበረው የምግብ እጥረት የዘንድሮውን በማነጻጸር አርባ በመቶ ያህል ብልጫ እንዳለው እነዚሁ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ይፋ ያደረጉት ጥናት ያሳያል፡፡

ከረሃቡ በስተጀርባ በርካታ ምክንያቶች ቢጠቀሱም ግጭት፣የኢኮኖሚ ውድቀት እና ድርቅ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የአለም ምግብ ፕሮግራም በተያዘው ዓመት 4ነጥብ4 ሚሊየን ደቡብ ሱዳናዊያንን ለመቀለብ እቅድ ቢኖረውም ረሃቡ እየከፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአገሪቱ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ በዚህ አመት እርዳታ ለማቅረብ እስካሁን ያገኘው ከስድስት በመቶ በታች የሆነውን ገንዘብ ነው፡፡

በዘንድሮው አመት ተመድ በደቡብ ሱዳን ለሚያቀርበው እርዳታ ከ1ነጥብ7 ቢሊየን ዶላር በላይ ያስፈልገኛል ማለቱ ተሰምቷል፡፡በደቡብ ሱዳን የሰብዓዊ እርዳታ በማቅረብ የአውሮፓ ህብረትን በመከተል ተመድ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ተመድ የአሜሪካ መንግስት በደቡብ ሱዳን ላይ ፊቱን በማዞሩ ምክንያተ ከሁለተኛ ደረጃ የእርዳታ አቅራቢነቱ እየተንሸራተተ ነው፡፡ አሜሪካ በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት እንዲኖር ፍላጎት አላት፡፡

ለዚህ የአሜሪካ ፍላጎት ተባባሪ አልሆን ባለው የሳልቫኪር መንግስት የጦር መሳሪያ እና የባለስጣናት እንቅስቃሴ ላይ ማዕቀብ በመጣል የትራምፕ አስተዳደር ጫና እያሳደረ ነው፡፡

አሜሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ያላትን ተጽኖ ፈጣሪነት እና የሁለቱ አገራት ማለትም በአሜሪካ እና ደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የግል ግንኙነት በመጠቀም በ ደቡብ ሱዳን ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመጣ እየሰራች ቢሆንም እስከ ወረሃ ግንቦት ድረስ 7 ሚሊየን ይደርሳል የተባለውን የደቡብ ሱዳን ተረጅዎች ቁጥር ማስተናገድ የሚችል ዝግጅት አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች  አድርገዋል ።(ምንጭ: ሲጂቲኤን)