የምስራቅ አፍሪካ እሳተገሞራ አፍሪካን ለሁለት ሊከፍል ይችላል – የስነ ምድር ባለሙያዎች

በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ   እየተብላላ የሚገኘው  እሳተ ገሞራ በሚያደርሰው የመሬት መሰንጠቅ  ቀጣናው ለሁለት ሊከፈል ይችላል  ሲሉ የስነ ምህዳር ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

 

በኬንያ ለዚሁ ማሳያ የሆነ ከባድ የመሬት መሰንጠቅ ተከስቷል፡፡

 

ለኬንያ መሬት መሰንጠቅ አደጋ የመሬት የታችኛው ክፍል መነቃነቅ እና እሳተ ጎመራ ውስጥ ውስጡን የሚያደርገው እንቅስቃሴ  ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

የስነ ምህዳር ባለሙያው ዴቭድ አዴድ በኬንያ ያለው ከባድ እና ተከታታይ ዝናብ ለመሬት መሰንጠቁ በዋና ምክንያትነት ሊጠቀስ አይችልም  ብለዋል፡፡

ባለሙያው በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ አከባቢ የሚታየው የእሳተ ጎመራ እንቅስቃሴ ከአሁኑ በጥናት ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል አለበለዚያ አደጋ ማስከተሉ የማይቀር ነው  ባይ ናቸው፡፡

ባለፈው  ሳምንት የጀመረው  ይህ የመሬት መሰንጠንቅ ግምቱ ያልታወቀ ነገር ግን ሰፊ ቦታን ያካለለሲሆን  በደቡባዊ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡

አፍረካ  በቀጣይ ሚሊየን አመታት ውስጥ ለሁለት እየተከፈለች እንደሆነ የሚነግረን እና በአከባቢው የሚኖሩ ሰዎችን  እንቅስቃሴ የሚገታ   መሆኑ የስምጥ ሸለቆው መሰንጠቅ አደጋዎች ናቸው፡፡

የአንድ አርሶ አደር  የእርሻ መሬት ላይመለስ ለሁለት መሰንጠቅ  የውሃ አቅርቦት መቋረጥ እና ከፍተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴ የነበረባቸው የኬንያ መንገዶች ከጥቅም ውጭ መሆን አገሪቱ ላይ የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅን  ተከትሎ የተስተዋሉ እውነታዎች ናቸው፡፡

የተፈጥሮ ክስተቱ  ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኬንያን መንግስት አስገድዶታል፡፡

የአገሪቱ የመንገድ ጥገና ባለስልጣን ሀላፊ ጁጉና ጋቲቱ  ሰዎች እንቅስቃሴው ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን አስጠንቅቀናል መንገድ በተሰነጠቀ ቁጥር ደግሞ ቁጥር ጥገና ለማድረግ ማሽኖቻችን ዝግጁ እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል፡፡

የመሬት መሰንጠቁ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ  መድረሻው  የት እንደሆነ ማወቅ አሳሳቢ ጉዳይ እና አጓጓጊ ጥያቄ ነው፡፡

 ስፋቱ እስከ 20 ሜትር የተገመተው የመሬት መሰንጠቅ ጥልቀቱን ያለቴክኖሎጂ እግዛበተፈጥሮ አይን ብቻ   የተሰነጠቀውን መሬት መጨረሻ ማየት አዳጋች መሆኑን ነው  የስነ ምህዳር ባለሙያዎች ያስቀመጡት፡፡

ስለመሬት መሰንጠቁ ግን የስነ ምህዳር ባለሙያዎች በሁለት ነገር እርግጠኛ ሆነዋል፡፡

 አንዱ የአፍሪካ ለሁለት መከፈል የሚሊየን አመታት እውነታ ስለመጀመሩ እና  በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ  የሚኖሩ ዜጎች በተፈጥሮ ክስተቱ የሚደርስባቸው ጉዳት እንደሚቀጥል ፡፡

ቢቢሲ እና በርካታ የኬንያ ብዙኋን መገናኛዎች ለጉዳዩ ሰፊ ትኩረት ሰጥተው ዘግበውታል፡፡