ግበጽ እና ኦስትሪያ በትምህርትና በሳይንስ ዘርፍ የአምስት አመት የፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ግበጽ እና ኦስትሪያ በትምህርትና በሳይንስ ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያሰችላቸውን የአምስት ዓመት የፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ትኩረቱን በአዳዲስ ግኝቶችና ቴክኖሎጂዎች ላይ አድርጎ በኦስትሪያ ቪየና በተካሄደውየ አፍሪካና አውሮፓ ህብረት ፎረምላ ይተሳታፊ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

በዚህ ወቅትም ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ክሩዝ ጋር በአለም አቀፋዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ከማድረጋቸው ባሻገር የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ይታወቃል፡፡

አልሲሲ በኦስትሪያቬና በነበራቸው ቆይታ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አሌግዛንደር ዳንደርቤልናንድ ጋር ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂደዋል፡፡

ሀገራቸውም በኢኮኖሚው መስክ ከኦስትሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ጠቅሰዋል ። (ምንጭ:  ኢጂፕት ኢንዲፔንደንት )