የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ በኩል ወጣቶች የበኩላቸው ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ ወይዘሮ ሙፈሪያት ተናገሩ

የአገሪቱን  ሰላም በማስጠበቅ በኩል ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚገባቸው ወይዘሮ ሙፈርያት ተናገሩ ።         

የሰላም ዋጋ እንዲሁ በቃል ተነግሮ ሊገለጽ እንደማይችል የገለፁት የሰላም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሙፋሪያት ካሚል ሰላምን ከማስጠበቅ አንፃር የወጣቱ ኃላፊነት ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

ሀገር በእናት ትመሰላለች የሚሉት በሰላም ሚኒስቴር የሚመራው የእናቶች የሰላም አምባሳደር ወጣቶች ስለ እናቶቻቸው እንደሚሳሱ ሁሉ ለእናት ሀገራቸው መሳሳት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ዜጎች በሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ይፈናቀላሉ ለአካል ጉዳት ይዳረገሉ፣ ለህልፈተ ህይወትም ይዳረጋሉ ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት እነዚህ ክስተቶች  ሆነው ቢያልፉም የሚያስከትለው ሁለንተናዊ ጉዳት ከአዕምሮ የማይጠፋ ጠባሳ ሆኖ ይቀራል ብለዋል ፡፡

በአገር ውስጥ በሰላም እጦት ምክንያት በሚደርሰው ጉዳትም በቅድሚያ ወጣቶች ሰለባ እንደሚሆኑ የጠቀሱት ወይዘሮ ሙፈሪያት ወጣቱ  በአጎራባች አገራት ውስጥ ግጭት  ካስከተለው ጉዳት  በመማር  ለአስተማማኝ ሰላም መሥራት እንደሚገባው አስተድተዋል ።

በዛሬው ዕለት በተደረገው ወቅታዊ የሀገሪቷ ሁኔታ በተመለተ ከመላው የሀገሪቷ ክፍሎች የተውጣጡ ወጣቶች ጋር የምክክር  መድረክም  ተካሄዷል ።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሰላም መድረክ ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የተውጣጡ ወጣቶች  የተሳተፉ ሲሆን ወጣቱ ሰላምን ከማረጋጋጥ አንፃር ያለበትን ሃላፊነት ትልቅ መሆኑን የተማሩበት መሆኑን ለዋልታ ቴሌቪዢን በሠጡት አስተያያት ተናግረዋል፡፡

በሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር እና በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ቁጥራቸው ከ1ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ምሁራን ተሳተፊ ሆነዋል ።

በሰላም  መድርኩ መጨረሻም ወጣቶች  ከአባቶች የወረሱትን የአብሮነት እና መቻቻል ባህልን በመውሰድ በዘር በቋንቋ፣ እና በኃይማኖት ሳይከፋፈሉ የሀገሪቷ ሰላም ለማስቀጥል ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመሆን ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡