በጎማ ከተማ ሶሰተኛው የኢቦላ ታማሚ ተገኘ

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሩዋንዳ አዋሳኝዋ ጎማ ከተማ ሶሰተኛው የኢቦላ ታማሚ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡

በዚህም ከቫይረሱ ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ ሩዋንዳ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷ ተነግሯል፡፡ ይሁንና የሩዋንዳ የጤና ሚኒስቴር ይህን አስተባብሏል፡፡

የ2 ሚሊየን ዜጎች መኖሪያ የሆነችው በሩዋንዳ አዋሳኝ አካባቢ በምትገኘው የዴሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ ሶስተኛዋ የአንድ አመት ሴት ልጅ የኢቦላ ቫይረስ ታማሚ መገኘቷን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡

ምንም እንኳ አሁን ላይ ህፃኗ በሆስፒታል ብትሆንም በትናንትናው ዕለት ህይወቱ ያለፈው አባቷ በበሽታው እንደተያዘ ከመረጋገጡ በፊት ከቤተሰቦቹ ጋር ለበርካታ ቀናት ቆይቷል ነው የተባለው፡፡

በዚህም ቫይረሱ ወደ ቤተሰቦቹ እና ሌሎች ያልታወቁ ሰዎች ተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ