በህንድ እኤአ በ2030 ከኤሌክትሮኒክስ ተሽከርካሪዎች ውጭ መጠቀም እንደማይቻል ውሳኔ አሳለፈች

ህንድ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ በ2030 በከተሞቿ ከኤሌክትሮኒክስ ተሸከርካሪዎች ውጭ መጠቀም እንደማይቻል ውሳኔ አስተላለፈች፡፡

አገሪቱ የተሸከርካሪ አምራች ኩባንያዎችንም ከሦስት ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክስ ተሽከርካሪዎች  ምርት እንዲገቡ አሳስባለች፡፡

የህንድን ኢንዱስትሪ እድገት ተከትሎ የአየር ንረት መበከል በዜጎቿ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያደረሰ ይገኛል፡፡ በአገሪቱ ከ1.3 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑት ዜጎቿ ስጋት ላይ መሆናቸውም ይነገራል፡፡

ጥናትን ዋቢ አድርጎ ሲ ኤን ኤን እንዳስነበበው ህንድ በአየር ንብረት መበከል በዓመት እስከ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች ሞት አበርክቶ አላት ይላል፡፡

በኒው ዴልሂ የሚኖሩ ህንዳውያን በቀን የሚተነፍሱት አየር በአማካይ እስከ አስር ሲጋራ እንደማጨስ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል ፡፡ 

ታድያ ዓለም በፓሪስ ከደረሰው ስምምነት ባሻገር የሀገሬው መንግስት ይህን ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

እኤአ  ከ2030 በኋላ በህንድ በነዳጅ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች አይኖሩም፡፡ ሁሉም በኤሌክትሪክ ባትሪ የሚሞሉ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡

በህንድ በተሸከርካሪ አምራችነት የተሰማሩ ድርጅቶች እኤአ ከ2020 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ምርቶቻውን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪ ማድረግ አለባቸው፡፡

ወደ ህንድ ተሸከርካሪ ለሚያስገቡም ይህ ህግ ተግባዊ ይደረጋል፡፡

መንግስት ይህን ውሳኔ ሲያስተላልፍ ለአየር ንብረት ለውጥ አንድ እርምጃ ነው ብሏል፡፡

ዘገባው የምጣኔ ሀብት ተንታኞች የህንድን ውሳኔ ይደግፋሉ ሲል ጽፏል፡፡ ህንድ በዚህን ጊዜ ውሳኔውን ማስተላለፏ አሜሪካንን ያስተምራታል ሲሉ፤ ለነዳጅ ላኪ አገራት ደግሞ ኪሳራን ያመጣል የሚሉ አሉ፡፡

ቢሆንም ግን አለማችን እየገጠማት ላለው ስጋት ይበል የሚያሰኝ እርምጃ ነው ብለዋል ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዓለም የታዳሽ ኃይልን እንድትጠቀም ጠቋሚ ነው ተብሏል ።