ታይላንድ   ከቱሪዝም  ዘርፍ  ባለፈው ወር ብቻ 3ነጥብ67 ቢሊዬን ዶላር ከዘርፉ ገቢ  ማግኘቷ ተገለጸ

ታይላንድ   ከቱሪዝም  ዘርፍ  ባለፈው ወር ብቻ 3ነጥብ67 ቢሊዬን ዶላር ከዘርፉ ገቢ  ማግኘቷ ተገለጸ ፡፡

ከደቡብ ኢሲያ በኢኮኖሚ አቅሟ በሁለተኛ ደረጃ የምተጠመጠው ታይላንድ የአኮኖሚ አቅሟን ከምንጊዜው በላይ  እያፈረጠመች ነው ።

ታይላንድ በቱሪስም አማላይ በመሆን የቱሪስቶችን ቀለብ ከመግዛት ባሻጋር በቢሊዬን የሚቆጠር ዶላርም እያጋበስች ትገኛለች፡፡

ታይላንድ የቱሪዝም እና ሰፖርት ሚኒስትሩ አንዳሉት ከሆነ በአጠቃላይ ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከአጠቃላይ ሃገራዊ ገቢው ባለፉት አመታት 4ነጥብ6 የነበረ ሲሆን አሁን ግን 6ነጥብ9 በመቶ ለማድረስ ተችሏል፡፡

 ባለፈው ወር ብቻ ተይላንድ  2ነጥብ59 ሚሊዬን የውጭ ሀገር ዜጎች  የጎበኟት ሲሆን በተለይ ደግሞ ከቻይና ከማሌዢያ ህንድ ሩሲያ እና ከአሜሪካ ሀገሪቷን  በመጎበኝት እና ትርፍ በማስገኘት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ታይላንድ ከእነዚህ ሀገራት ቱሪስቶች 125 ቢሊየን የታይላንድ ባሃት አልያም 3ነጥብ67  ቢሊዬን ዶላር አግኝታለች፡፡

 ታይላንድ ባለፈው አምስት ወራት ብቻ ደግሞ ከቱሪዝም ዘርፉ 747  ቢሊዬን ባሃት አግኝታለች፡፡

አንድ የአሜሪካን ዶላር 34 ነጥብ 02 የታይላንድ ባሃት ነው የሚሸጠው፡፡

የባሃት የመግዛት አቅም እንዲያንሰራራ ከቱሪዝም ሀብቱ የሚገኛው ሀበት  እና አሁን ያለው እንቅስቃሴ ይበልጥ ያጠነክረዋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

በታይላንድ ዩሮ ዶላር እና ፐውንድ  በገንዘብ ገበያው ላይ እየተነሸራሸሩ መገኘታቸው እንደ ስጋት ቢታይም የታይላንድን  ኢኮኖሚ ከመገባት አንፃር ግን  ገቢው ከፍተኛ ድርሻው ይውስዳል፡፡ የታይላንድ ኢኮኖሚ አሁን ባለው ሁኔታ በ12 በመቶ እያደገ ነው፡፡