ዓለም  ባንክ በቻይና ሰባት ከተሞች ላይ የግል መኪኖችን ለመቀነስ  ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ

የዓለም ባንክ ወደ ሰባት በሚደርሱ የቻይና ዋና ዋና ከተሞች ላይ የግል መኪኖችን በመቀነስ የህዝብ ማጓጓዣ የትራንስፖርት  አማራጮችን በማብዛት የትራፊክ መጨናነቁን ለማሳለጥ የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡

በዓለም ባንክ ለትራፊክ ማሳለጫ የሚሆን ገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ውሳኔ ያገኙት የቻይና ከተሞች ቤጂንግ፣ ታንጂን, ኒንጎ, ኒንቻንግ እና ሼንዜንን ጨምሮ በጠቅላላው 32ነጥብ 73 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሆነው ግሎባል ኢንቫይሮመንት ፋሲሊቲ በተሰኘ ተቋም የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም በኩል በተገኘ ድጎማ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የዓለም አቀፍ ገንዘብ አበዳሪው እንደሚለው የመሬት አጠቃቀምን እና ትራንስፖርትን በማካተት የከተማ ፕላንን ካለው የመሬት ቆዳ ሽፋን ጋር አቀናጅቶ ለመሥራት ፈንድ መደረጉንም  ገልጿል፡፡

በተሸከርካሪዎች የሚፈጠረውን መጨናነቅ ለመቀነስ እንዲሁም በመናሃሪያዎች አካባቢ የሚስተዋለውን የእግረኞችና የብስክሌት ተጠቃሚዎችን መተላለፊያ እጥረቶችን ለመፍታት ገንዘቡ ፈንድ መደረጉ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል።

በአለም ባንክ የከተሞች ኢኮኖሚስትና ፕሮጀክት ምክትል መሪ የሆኑት ፋንግ ዋንሊ፡፡

ፕሮጀክቱ ከተማዎች የተቀናጀ የከተማ ፕላን ለማውጣት ፖሊሲዎችን, መመሪያዎችን እና ስልቶችን የመገንባት ችሎታቸውን እንዲያጠናክሩ ይረዳቸዋል ነው የተባለው፡፡

የቻይና ከተሞች በ2016 ከነበረው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት ወደ 57ነጥብ 35 በመቶ   የሚሆነው  ህዝቧ በከተሞች እንደሚኖር የዓለም ባንክ መረጃ ያሳያል፡፡ ይህ ቁጥር  እኤአ በ 2030 ወደ 70 በመቶ እንደሚያድግም ተገምቷል፡፡

ይህን መሠረት በማድረግ ቻይና  የከተሞች ፕላኗን ማሻሻል እና ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ ከተሞች መፍጠር መስራት የቻይና ቀጣይ ፈተናዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ የአለም ባንክ መረጃ ያሳያል፡፡

የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ ደግሞ የቻይና የምትከተለው አዲስ የከተሞች ፕላን ሰዎችን ማዕከል ያደረገ ዕድገት ለሰዎች ምቹ የሆነ አሠራር መሠረት ያደረገ  እንደሆነ ነው የገለፀው፡፡

እ.ኤ.አ በ1991 የተመሠረተው የጂኢኤፍ ግሎባል ኢንቫይሮመንት ፋሲሊቲ የተሰኘው  የፋይናንስ ድርጅት ዋና አላማ  የአካባቢ ጥበቃ ችግሮችን ለመቅረፍ ሲሆን  በ 790 ሀገራት ውስጥ 120  ኢንቨስትመንቶችንና መርሃግብሮችን መተግበሩን ተገልጿል፡፡( ምንጭ:ዥንዋ)