አሜሪካ በምጣኔ ሃብቷ እድገት ላይ ለምታቀርበዉ ትችት ቻይና ተቃዉሞዋን እያሰማች መሆኑ ተገለጸ

አሜሪካ በቻይና ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ላይ ለምታቀርበዉ ትችት ቻይና ተቃዉሞ ዋን  እያሰማች መሆኑ ተገለጸ ፡፡

በኢስያ አህጉር ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ላይ የምትገኘው  ቻይና የአለም ንግድ ድርጅት አባል የሆነችዉ እ.ኤ.አ ከ2001 ጀምሮ ነዉ፡፡

ሆኖም እያስመዘገበችዉ የሚገኘው ምጣኔ ሃብታዊ እድገት የአሜሪካን ሃያልነት የሚገዳደር መሆኑ እረፍት የነሳቸዉ የዋሺንግተን መሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በዚህች ሩቅ ምስራቃዊት ሃገር ምጣኔ ሃብት ላይ ተፅእኖ ለማሳደር መሞከራቸዉ አልቀረም፡፡

ሰሞኑን ደግሞ የዋሽንግተኑ የንግድ ተቋም ተወካይ ሮበርት ላይዘር የቻይና ጉዳይ በአለም ንግድ ድርጅት በአንክሮ የሚከታተሉት ጉዳይ መሆኑን ለተቋሙ መግለፃቸዉ ቻይናን አስቆጥቷል፡፡

የቻይና የንግድ ሚኒስቴር አሜሪካ የቻይናን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለመቀበል አለመፈለጓ እና በተለያዩ የዓለም አቀፍ መድረኮች ዋሽንግተን ስለ ቻይና ያላት አሉታዊ አቋም ማንጸባረቋን ተቃውሟል፡፡

በተያያዘም የአዉሮፓ ህብረት ለድርጅቱ ባቀረበዉ ሪፖርት ለቻይና ኢኮኖሚ  ተገቢዉን እዉቅና አለመስጠቱን እና አሜሪካም ለንግድ ድርጀቱ ቅሬታ በማሰማት ላይ እንደሆነች ከቤጂንግ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

በንግድ ድርጅቱ የአዉሮፓ ሀገራት ተለዋጭ አባል በሚያካተቱበት ሁኔታ የተመከረ ሲሆን በመድረኩ አሜሪካ የቻይናን ኢኮኖሚ ሁኔታ የሚቃወም ሪፖርት አቅርባለች ነዉ የተባለዉ፡፡

የበርካታ ተለዋጭ አባል አገራት የቆይታ ጊዜ በመጪዉ ሳምንት የሚጠናቀቅ ሲሆን በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 15 መሰረት ቻይና ለ16 አመታት የሽግግር አባል ሆና የቆየችበት ጉዳይ ጥያቄ  ምልክት ዉስጥ ነዉ ተብሏል፡፡ 

ቻይና ከኢኮኖሚዋ ጋር በተያያዘ ለተነሳዉ ዉዝግብ የአለም አቀፉ ንግድ ድርጅት ሁነኛ ህግ አለማስቀመጡ በዋናነት የሚጠቀስ ቢሆንም ክስተቱ ምንም ጉዳት አያስከትልም ሲል የቻይና ንግድ ሚስቴር አስታዉቋል፡፡

አሜሪካ የአለም አቀፉን ንግድ ተቋም አሰራር አሻሽላለሁ በሚል ሰበብ የገበያና ኢኮኖሚ ሁኔታን ለመቀየር እየሞከረች መሆኑንም ሚኒስቴሩ ጠቁመዋል፡፡/ሲጂቲኤን/