በብሪታኒያ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ማስመዝገቡ ተገለጸ

በብሪታኒያ የነዳጅ ሽያጭ በሦስት ዓመት ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን  የዋጋ ጭማሪ  ማስመዝገቡ ተገለጸ ።

በሀገሪቱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ለሦስት አመታት  ለነዳጅ  ከፍለው የማያውቁትን  ጭማሪ በመክፈል አዲሱ ዓመታቸውን እንደሚጀምሩ የተለያዩ  መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በዚህም ያልተጣራ አንድ ሊትር ነዳጅ እ.ኤ.አ በ2018 አዲስ ዓመት አንደኛ ወር በአማካይ በበርሜል ከሚሸጠው 120  ነጥብ 66 ፓውንድ በቀጣዩ ወር የነዳጅ ዋጋው ወደ 121 ነጥብ 11 ፓውንድ ከፍ ይላል ነው የተባለው፡፡ 

ይህም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው እ.ኤ.አ ከታህሳስ 2014 ጀምሮ ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የነፍጣ ዋጋም በርሜል ከ1መቶ 21 ነጥብ 11 ፓውንድ ከነበረበት ወደ 123 ነጥብ 46 ፓውንድ ከፍ ብሏል፡፡

እንደ መረጃዎቹ ከሆነ የነዳጁ ሽያጭ ዋጋ ከፍ በማለት በአንድ በርሜል 66 ነጥብ 61 ዶላር ጭማሪ በማሳየት በግንቦት ወር 2015 ላይ በከፍተኛነት ተመዝግቧል፡፡

በታህሳስ ወር የተሸጠው የነዳጅ ዘይት ክምችት ከሁለት አመት ከ6 ወር የቆየ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሞተረኞች ፓምፕ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል ተብሏል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ በ2018 የሞተር ፓምፑን በቀላል ዋጋ ለማግኘት አዳጋች እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡

በዝቅተኛ ዋጋ ይሸጥ የነበረ ነዳጅ ዋጋ በመጠናቀቅ እና በምርቱ ጭማሪ በማሳየት የኦፔክ ነዳጅ አምራች ኩባንያ የዓለም አቀፍ ነዳጅ ገበያን ሁኔታ ተፅዕኖን በመቀነስ  የሚፈለገውን ውጤት በመምጣት ላይ እንደሚገኝ  እና የበርሜል ነዳጅ ሽያጭ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዳይደረግ ግፊት  ለማድረግ  እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡  

የተቀናጀ የዘይት እና የነዳጅ ማደያ (ፎርቲስ ፓይፕላይን) ለብሪታኒያ ገበያ በቀን ከግማሽ ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የሚያቀርብ ሲሆን  በማስተላለፊያ ቧንቧ ውስጥ ስንጥቅ በመከሰቱ ከታህሳስ ወር ጀምሮ  ለጥገና መዘጋቱ ነው የተገለጸው፡፡

ይህም ለቤት መኪኖች በአማካይ 55 ሊትር ነዳጅ ለመሙላት 66 ነጥብ 61 ፓውንድ ወጪ በማስወጣት በሐምሌ ወር ከነበረው ሽያጭ በ7 ነጥብ 73 ፓውንድ ከፍ አድርጓል ተብሏል፡፡