የሺሞን ፔሬዝ የቀብር ስነ-ስርዓት በእየሩሳሌም ተፈጸመ 

የቀድሞው የእስራኤል ፕሬዝደንት ሺሞን ፔሬዝ የቀብር ስነ-ስርዓት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ በርካታ የአለም መሪዎች በተገኙበት በእየሩሳሌም ተፈጸመ፡፡

ባራክ ኦባማ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፔሬዝ ለሃገሪቱ እድገትና ለመላው አለም ሰላምና መረጋጋት የተጉ መሪ እንደነበሩ እንስተዋል፡፡

የፍልስጤሙ መሪ ማህሙድ አባስም በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ ሲሆን እ.ኤ.አ 2010 ወዲህ ወደ እስራኤል ሲገቡ የመጀመሪያቸዉ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፤ የአውሮፓ ህብረት፤የጀርመን ፤ የፈረንሳይ ፤የጃፓን፤ የሩሲያ፤ የጣሊያን፤ የአውስትራሊያ፤ የካናዳ፤ የኔዘርላንድ፤ የስፔን፤የጆርዳንና የሜክሲኮ መሪዎችና ተወካዮች በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ ከተገኙት መካከል ናቸው፡፡

አንጋፋው ፖለቲከኛ ሺሞን ፔሬዝ ለአይሁዳዊቷ ሀገር እስራኤል እ ኤ አ 1948 መመስረት ትልቁን ድርሻ ከሚወስዱ ፖለቲከኞች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል ላበረከቱት የሰላም ድርድር ሚና እ ኤ አ 1994 የኖቤል ሰላም ሽልማት ማግኘታቸውም ይታወቃል፡፡

ሺሞን ፔሬዝ ከፕሬዝደንትነት ስልጣናቸው እንደአውሮፓ አቆጣጠር በ 2014 ላይ ነበር በጡረታ የተገለሉት፡፡

ምንጭ፡  ሲ ኤን ኤን