ፍርድቤቱ የትራንፕን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉ ለሙስሊም ሀገራት ዜጎች ለግዜው እፎይታን መፍጠሩ ተመለከተ
ትራምፕ ለሽብር ስጋት ካሏቸዉ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ ኢራን፣ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ እና የመን ለ30 ቀናት የይለፍ ወይም ቪዛ ፈቃድ ጥያቄ እንዲያዝ የሚያደርግ መመሪያም እያወጡ መሆናቸውን መገለጹ ይታወቃል ።
እነዚህ ሰባት ሃገራት ዜጎች ለጊዜዉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ያሳለፉት ዉሳኔ በፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ ለሀገራቱ ዜጎች ጊዜያዊ እፎይታን የፈጠረ መስሏል።
ሳንፍራንሲስኮ ግዛት በሚገኘዉ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ዉሳኔዉን ለማስቀልበስ ያቀረበዉ አቤቱታ በድጋሚ በፌደራሉ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ በሀገሪቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል።
ጉዳዩ ወደ ሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰደ ሲሆን ክርክር እንደሚካሄድበት ይጠበቃል።
የፕሬዝደንቱ ዉሳኔ ከሀገሪቱ ሕግ እንደሚፃረር የሚገልፁ ወገኖች ፍርድ ቤት የሀገሪቱን መሪ ዉሳኔ መጣል የቻለዉ የሕግ የበላይነት ያለባት በመሆኗ እንደሆነ ይናገራሉ ።
ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት ስደተኞችን እንደማይቀበሉ እና በሕገወጥ የገቡትንም አባርራለሁ በማለት መዛታቸው ይታወሳል -(ዶችዌለ)።