ፕሬዚዳንት ዱቴርቴ ፈተናዎችን በመጋፈጥ የሥልጣን ዘመናቸውን ማቆየታቸው ተመለከተ

የፊልፒንስ  ፕሬዚዳንት  የሆኑት ሮድረጎ ዱቴርቴ  የተለያዩ  የውስጥና የውጭ  ፈተናዎችን  በመጋፈጥ  ለአንድ ዓመት ያህል የሥልጣን ዘመናቸው ሳይነቃነቅ ማቆየት መቻላቸው  ተገለጸ ።        

አወዛጋቢው እና በግራ አጋቢ ንግግራቸው የሚታወቁት፤ የቀድሞው የዳቫኦው ከተማ ከንቲባ የአሁኑ 16ኛው የፊሊፒንስ ፕሬዝደንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ፤ 12 ወራትን በፕሬዝደንትነት መንበራቸው አሳልፈዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ገና ከመነሻቸው ነበር የዓለምን ቀልብ ለመሳብ የቻሉት፡፡ የሚያነሷቸው ሀሳቦች እና የሚሰጧቸው አስተያየቶች እንዲሁም የሚሰነዝሩት ቃላት ዓለም ትኩረት እንዲሰጣቸው  በቀላሉ ያስቻለ ነበር፡፡

ፖልስተርስ የተሰኘው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት በማካሄድ የሚታወቀው አለማቀፉ ተቋም ይፋ እንዳደረገው ሰውየው 80 በመቶ በሚሆኑት ዜጎቻቸው ስለ አመራራቸው እና የፖለቲካ አቅማቸው አመኔታን አትርፈዋል ይላል፡፡

ምንም ይሁን ምን ዱቴርቴ እከውነዋለሁ ካሉ ያደርጉታል ሲሉም ፊሊፒናውያን አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ ኩራት ይሰማቸዋል ሲል አስፍሯል፡፡

ለዚህም ነው አንድ ዓመት ያስቆጠረውን ምርጫ በአገሬው ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአብላጫ ድምፅ ሊያሸንፉ የቻሉት፡፡

ሰውየው የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ይዘዋቸው የመጧቸው ፖሊሲ እና ስትራቴጂዎች፤ ለዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ የህዝቡን ጥያቄዎች እንደ እርሳቸው አገላለጽ በአጭር ጊዜ ውስጥ እከናውለሁ ማለታቸው ይበልጥ ተቀባይነታቸውን ጨምሮላቸዋል፡፡

በፊሊፒንስ ወጣቱን ለጥፋት የዳረገው እና አገሪቱም ተረካቢ ዜጋ እስከማጣት ስጋት ላይ እስክትወድቅ ያደረሳትን የአደንዛዥ እጽ ገበያ መበጣጠስ ፤ አለማቀፉን የአሸባሪ ቡድን አይ ኤስን ጨምሮ የተለያዩ ቡድኖች ትኩረት እየሆነች የመጣቸውን አገራቸውን ከጥፋት መታደግ እና ብሎም አሸባሪዎችን ከሌሎች አገራት ጋር በጋራ በመሆን ለመታገል ቁርጥ አቋም እንዳላቸው ለህዝባቸው በአደባባይ የተናሩት ነበር፡፡

የህዝቡን ጥያቄ የማያስተናግዱ ለአመታት የተተበተበው የሙስና ሰንሰለት በእሳቸው የስልጣን ዘመን እድሜው አጭር እንደሚሆንም የአሁኑ ፕሬዝደንት ከ12 ወራት በፊት እንዲመረጡ ሊተገብሯቸው የገቧቸው ህዝባዊ ቃል ኪዳናቸው እንደነበር  አልጀዚራ ጽፏል፡፡

አሁን ግን ፕሬዝደንቱ 365 ቀናትን በስልጣን አሳልፈዋል፡፡ ምንም እንኳ እቅዶቻቸው እረጅም አመታትን የሚፈጁ  እና በሂደት የሚፈቱ ቢሆንም ከገቧቸው ቃሎች መካከል ዋና ዋናዎቹን ግን አልፈፀሙም ሲሉ ተቃዋሚዎቻው ከሰዋቸዋል ነው የተባው፡፡

ፕሬዝደንቱ 297 መቀመጫ ባለው የህዝብ ተወካዮች ፊት ቀርበው ለቀረበባቸው ክስ ምክንያት ለመስጠት ሞክረዋል፡፡ ከአጠቃላዩ የፓርላማው መቀመጫ ተቃዋሚዎች 59 ወንበር ብቻ ነው ያላቸው፡፡ ነገር ግን የቀረበው ጥያቄ የእነርሱዉ ብቻ አልነበረም፡፡

ቀድሞ ሓሳባቸውን ሲደግፉ የነበሩ አጋፋሪዎቻው እና የእርሳቸው ወገን የነበሩ ነገር ግን በተወሰነ የአቋም ልዩነት ውስጥ የነበሩ ወዳጆቻውም ከወዲያኛው ጎራ ቆመዋል ነው የተባለው፡፡

ይህ የሰውየውን የአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታ በድክመት እንዲገመገም ያስቻለ ነው ተብሏል፡፡

እንደ አልጀዚራ ሰውየው አሰራራቸውን መልሰው እስካልፈተሹ እና ለተፈፃሚነቱ ካልቆሙ ስልጣናቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይደርሳል ሲሉ የሚተነትኑ እንዳሉ ያስነብባል፡፤

እወዛጋቢው ሰውዬ ውጫዊ ውዝግብ ሲፈጥሩ በአገራቸው ሌላ ውዝግብ ተፈጠረ ሲሉ የተሳለቁም አልጠፉም ነው የተባለው፡፡

ቢሆንም ግን አሁንም ህዝቡ በሮድሪጎ ዱቴርቴ ያምናል፡፡ ሰልጣናቸውን በአግባቡ እና በትክክል እንደሚጠቀሙም ተስፋ አለው፡፡ ሰውየው ደግሞ በዚህ አይታሙም እየተባለ ይገኛል፡፡ ቢሆንም ግን የገቡትን ቃል ለመፈፀም መትጋት ይኖርባቸዋል የሚል አስተያየት የሚሰጡ ፊሊፒናውያን አልጠፉም ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡