የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ቻይና ገብተዋል

ኢማኑኤል ማክሮን በቻይና በሚያደርጉት የሶስት ቀን ቆይታ ጥንታዊ የቻይናን ከተሞች የሚጎበኙ ሲሆን የሁለቱን አጉራት  ግንኙነት ለማሳደግ በሚረዳው የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም እየተነገረ ይገኛል፡፡

የቻይና እና ፈረንሳይ የሁለትዮሽ  ግንኙነት የ ጀመረው ከ17ኛው እና 18 ኛው ክፍለዘምን ጀምሮ እንደነበር በታሪክ ይናገራል፡፡ በወቅቱም ሀገራቱ በንግድ እና በፖለቲካ ጉዳይ የጋራ መድረክ እንደነበራቸውም  ነው የሚነገረው፡፡

ይሁን እንጅ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ የዘመን ቀመር በ1900 ኃያላን የአዉሮፓ ሀገራት በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ ያላቸዉን የቅኝ ግዛታቸዉን ያስፋፉ ነበር፡፡ ፈረንሳይ ከእነዚህ ሃያላን ሀገሮች መካከል አንዷ የነበረች ስትሆን በወቅቱ ፈረንሳይ ቻይናን በመውረሯ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሻክሮት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ114 ክፍለ ዘመን በነበረው የሃን ዳይነስቲ የተመሰረተው የንግድ መስመር የኢሲያዉን ምድር ከአፍሪካ እና የአዉሮፓ ሀገራት በንግድ፣ ማህበራዊ እና በፖለቲካ እንዲያስተሳስር ታስቦ የተመሰረተ ነው፡፡

በዚህ የንግድ መስመር ላይ በተለይም ቻይና ሁለቱ ኮሪያዎች እና ጃፓን የጥጥ ምርቶችን በማቀርብ አለምን ያዳርሱ ነበር፡፡

ታዲያ ይህ የንግድ ቀጠና የኢስያዉን ምድር ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር የሚያገነኝ በመሆኑ በቀጠናው ላይ ያሉ ሀገረት የይገባኛል ጥያቄያቸው እያደገ ሲመጣ የደቡብ ኮሪያን ባህረ ሰላጤን ጨምሮ ጥያቄው እያደገ  መጣ፡፡ ይህም በቀጠናው ላይ ውጥረትን ማንገስ ጀመረ፡፡

በተለይ የፈረንሳይ ቻይናን መውረር ተከትሎ በተለያዩ ጊዜ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለመጠገን ሙከራ ይደረግም ነበር፡፡ ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነትም “ሲኖ ፈራንስ” የሚል ስያሜ ተሰቶትም ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ከቀዝቀዛው ጦርነት በኋላ ፈረንሳይ ለቻይናው ኮሚንስት ፓርቲ እውቅና እንደማትሰጥ አስታወቀች፡፡ ይልቁንም ቻይና በግድ እያስተዳደረቻት እንደምትግኝ የሚነገርላት እና ራሴን ልቻል የሚልን ጥያቄ ለምታነሳው ታይዋን ድጋፍ ማድረግ ጀመረች፡፡

ይህ እና ሌሎች ውጥረቶች የኤሲያዉን ምድር ከአዉሮፓው ጋር አቆራረጠው፡፡ የሃር መንገድ ወይም “ሲልክ ሮድ” የሚል ስያሜ የነበረው ጥንታዊው የንግድ ቀጠናም ታሪክ ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ ይልቁንም ይህን የንግድ መስመር ቻይና በበላይነት ይዛው ፊቷን ወደ አፍሪካ አዙራለች፡፡ የሁለቱ አህጉራት ግነኙነት በመቀዛቀዙ የማንም የአዉሮፓ ሀገር መሪ በተለይም የቻይናን ምድር እንዳይረግጥ የቻይናው ኮሚንስት ፓርቲ ከለከለ፡፡

አሁን የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ትዝ አለኝ የጥንቱ ይመስል የሶስት ቀን ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ በጂንግ ሲገቡ ፕሬዝዳንት ዢን ፒንግ ሞቅ ባለ ደስታ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ኢማኑኤል ማክሮን በቻይና በሚያደርጉት የሶስት ቀን ጉብኝት የ5ሺህ ዕድሜ ያለዉን የቴራኮታ ጦረኞችን ሙዚየም ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን ከአቻቸው ዢን ፒንግ ጋር ጥንታዊዉን “ሲልክ ሮድ” ድጋሚ መገንባት በሚለው ላይ ውይይት ያደርጋሉ፡፡

ይህ የማክሮን እቅድ የእስያዉን ምድር ከአዉሮፓ ጋር በመንገድ፣ በባቡር መስመር እና በባህር የሚያገናኝ ነው፡፡

ይህም ፕሮጀክት ከ1 ነጥብ 33 ትርሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ያስፈልገዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከዚህም በተጨማሪ አሜሪካ እምብዛም ትኩረት ላልሰጠችው የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ በገራራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለቸው ገልፀዋል፡፡

ቻይና አንድ መቀነት አንድ መንገድ ወይም በኢንግልዘኛው “ዋን ቤልት ዋን ሮድ” በሚለው አዲሱ እቅዷ መካከለኛው እስያ ከህንዱ ውቅያኖስ እና ቀይባህር ጋር በባቡር ለማስተሳሰር እየሰራች ትገኛለች፡፡

እንደባለሙያዎች ትንትና ሁለቱ ሀገራት ከሁለትዮሽ ግንኙነታቸው በተጨማሪ በአሜሪካ የበላይነት ብቻ በተያዘው በወቅታዊ የዓለም ጉዳይ ላይም ይመክራሉ፡፡