የየመን አማጺያን አብዛኛውን የኤደን ከተማ እየተቆጣጣሩ እንደሚገኝ ተገለጸ

የየመን አማፂያን አብዛኛው የኤደን ከተማ ክፍሎችን እየተቆጣጠሩ መሆኑ ተገለጸ ።

የፕሬዚደንት አብዱራቡ መንሱር ሃዲ ቤተመንግስትን ጨምሮ በኤደን ከተማ የመንግስት የተለያዩ  የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም  በአማፂያኑ ተከበዋል፡፡

አንዳንድ ባለስልጣናት ወደ ሪያድ ያቀኑ ሲሆን ጠቅላይ ሚስትሩም ቢሆኑ በዝግጅት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

የአረቡ ማዕበል እስካሁን ድረስ የዘለቀባት የመን፤ ለዜጎቿ የስጋት ቀጣና ስለመሆኗ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሸን ሪፖርት በወጣ ማግስት ነው መቀመጫውን በደቡብ የአገሪቱ ክፍል ያደረገው የፕሬዚደንት አብዱራቡ ማንሱር ሃዲ መንግስት አገሪቱን ለቆ ስለመውጣት  እየተዘጋጀ የሚገኘው ።

የመንን ለመከፋፈል የሚንቀሳቀሱ አማፅያን የወቅቱ የሀገሪቱ መንግስት መቀመጫ የሆነውን  የኤደን ከተማን በመቆጣጠራቸው ምክንያት  ነው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አገሪቱን በመልቀቅ ላይ ይገኛሉ  

የፕሬዚዳንት አብዱራቡ ማንሱር ሃዲ መቀመጫ የሆነችውን ኤደን ከተማ፤ ባሳለፍነው ቅዳሜ አዲስ ውጊያ  መደረጉን ተከትሎ ነው አማፅያን የኤደን ከተማን የተቆጣጠሩት።

አማፅያኑ የፕሬዚዳንቱን ዋና መሥሪያ ቤትንም መቆጣጠራቸውን ነው ዓለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በአሁኑ ወቅት እየተቀባበሉት  ነው ።

የየመን ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ቢን ሴት ልጅ፤ አማፅያኑ በኤደን ከተማ የሚገኘውን የመንግስት ዋና መቀመጫ እንዲቆጣጠሩና የመፈንቅለ መንግስት እንዲሞክሩ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግሥት ድጋፍ አድርጓል በሚል ትከሳለች። 

 ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ቢን በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጦር በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በኤደን ከሳለፍነው ቅዳሜ ጀምሮ የተፈጠረው ቀውስ አገሪቱን ወደ የተባባሰ ችግር እንዳያስገባት ተሰግቷል።

የባህር ሰላጤው ሀገራት በኤደን የሚካሄደው ውጊያ ረገብ እንዲል ለተፋላሚ ሃይላት ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ  ጥሪ በማስተላለፍ ላይ እንደሚገኙ   ቢቢሲ ዘግቧል።

ሆኖም ሁቲዎችም ሆኑ አማፂያኑ ከመተላለቅ ወደኋላ እያሉ አይደለም፡፡ ታይም መጽሔት በገፁ ላይ እንዳሠፈረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤደንን ለቀው ሊወጡ እንደሆነ ሲጠቅስ አብዛኛው ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ወደ ሪያድ እንዳቀኑ ጠቅሷል፡፡

ኒውዮርክ ታይምስ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ ጽህፈት ቤታቸው በአማፂያን በመከበቡ ስጋት ውስት እንደሚገኙ አስነብቧል፡፡

የአሁኑ የየመን ጉዞ በበርካታ መንግስታት እና ዓለማቀፍ ተቋማት ዘንድ አፋጣኝ ምላሽ የሚቸርበት ጊዜ ስለመሆኑ እየተነገረ ሲሆን የፖለቲካ ተንታኞችም አገሪቱ ወደለየለት ቀውስ እያመራች ስለመሆኑ ነው የሚጽፉት፡፡

እኤአ በ2015 በሁቲዎች ግፊት መቀመጫው የነበረችውን ሰሜናዊቷን ሰነዓን ለቆ የወጣው የፕሬዚደንት አብዱራቡ ማንሱር ሃዲ አስተዳደር አሁን ደግሞ ለአማፂያኑ ኤደንን ሊተውለት ነው፡፡

ይህ ደግሞ ከዓመታት በፊት የመን ስትተዳደር ወደነበረው ሰሜን እና ደቡብ ግዛት አስተዳደሯ ትመለሳለች የሚሉ የፖለቲካ ተንባዮችም መደመጥ ጀምረዋል፡፡