በህንድ ሁለት ሦስተኛው ህዝብ ለአየር መተንፈሻ ችግር እየተጋለጠ መሆኑን ጥናት ጠቆመ

በህንድ ሁለት ሶስተኛው ከሃገሪቱ ህዝብ በአየር መተንፈሻ ችግር እየተጠቃ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ ፡፡

በህንድ የተሠራው አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከአጠቃላይ የሃገሪቱ ከሚኖረው 1ነጥብ 3 ገደማ ከሚሆነው ህዝብ መካከል አብዛኛው በገጠራማ የሃገሪቷ ክፍል የሚኖር ሲሆን  ከእነዚህም ውስጥ በአየር ብክለት ምክንያት ለከፍተኛ የመተንፈሻ ችግር የተጋለጡ ናቸው፡፡ 

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃን ዋቢ ያደረገው ጥናቱ በዓለማችን በአየር ብክለት ደረጃ ውስጥ ካሉት ከተሞች መካከል የህንድ ከተሞች የሚመደቡ ሲሆን በህንድ ከተሞች  የአየር ብክለት  ዋነኛ የመወያያ አጀንዳም ሆኖ ይገኛል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የዓለም የሳይንትስት ቡድን፣ የሀገሪቷ ኤክስፐርቶችን እና የኢንዲያን የቴክኖሎጂና ጤና ዩንቨርሲቲ የጥናት ውጤት መሠረት በማድረግ እኤአ ከ2015 ጀምሮ በሀገሪቷ የነበረው ሞት ከአየር ብክለት ጋር የተገናኘ እንደሆነ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ይህ ችግር ደግሞ በከተማዋ ብቻ ተወስኖ የቀር እንዳልሆነ ያመለከተው ሪፖርቱ በተለይም የሃገሪቷ የገጠር ክፍሎች የሚገኙ ነዋሪዎች ክፉኛ ተጠቂዎች እየሆኑ ነው፡፡

በችግሩ ከተጠቁት  ህዝቦች መካከል ደግሞ  2 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በገጠራማ አካባቢ የሚኖር እና የችግሩ ሰለባ የሆነ ነው፡፡

በተለይም እኤአ በ2015 ብቻ በነበረው ሞት 25 በመቶ የሚሆነው በአየር ብክለት የተከሰተ መሆኑን  የጥናቱ ሪፖርት ገልጿል ፡፡

በሀገሪቷ የአየር ብክለትን የሚጨምሩ ኩባንያዎች አብዛኞዎቻቸው ከመንግስት እውቅና ውጭ በመሆናቸው ችግሩን እያባሰው ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት ትኩረት የማይሠጠው ከሆነና እና ችግሩ ካለተገታ ከችግሩ ጋር በተገናኘ የሚሞቱት የሰው ቁጥር እኤአ እስከ 2030 ወደ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ገልፀዋል፡፡

ለችግሩ አስገዳጅ ህግ ከወጣ እና ችግሩን መቀነስ ከተቻለ ሊደርስ የሚችለውን ሞት በ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዝቅ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡( ምንጭ :ሲኤን ኤን)