በኢንዶኔዠያ በደረሰው ርዕደ መሬት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1ሺህ 234 ደረሰ

በኢንዶኔዠያ በተመዘገበው 7 ነጥብ 5  የመሬት ርዕደ መሬት ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 234 መድረሱን  የሀገሪቱ  መንግስት አስታወቀ።

በሱላዌሲ በተባለችው ደሴት በተከሰተው ርዕደ መሬት ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር  ከ844  ወደ 1 ሺህ 234 ከፍ ማለቱ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

በጉዳቱ አስካሁን 200 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋለው አሰቸኳይ አርዳታ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፤ የሟቾች ቁጥር ከዚም ሊቸምር አንደሚችል በመነገር ላይ ነው፡፡ ርዕደ መሬቱ ያስከተለው ያስከተላውን ተክክለኛ ጉዳት ለማወቅ አሁን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪ እንዳደረገው ታውቋል።

በርዕደ መሬቱ በአንድ አካባቢ ብቻ የሚገኙ 1 ሺህ 700 ቤቶች  የወደሙ ሲሆን በመኖሪያ ቤቶቹ ከነበሩት ውስጥ 100 የሚሆኑት ሳይቀበሩ እንዳልቀረ ተነግሯል፡፡  (ምንጭ:ቢቢሲ )