ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተንሸራቶ ወንዝ ውስጥ ገባ

ንብረትነቱ የአሜሪካን ሚያሚ ግዛት የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር በዕለቱ በነበረው ነጎድጓዳማ ዝናብ ምክንያት ተንሸራቶ ፍሎሪዳ በሚገኘው የቅዱስ ዮሐንስ ወንዝ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡

አውሮፕላኑ 143 ተሳፋሪዎችን በመያዝ ከኩባ ከጓንታናሞ ቤይ ወደ ወታደራዊ ከተማዋ ጃክሰንቫይል ሲጓዝ የነበረ ቢሆንም በተሣፋሪዎቹ ላይ የከፋ ጉዳት አለመድረሱ ታውቋል፡፡      

በአደጋው በትንሹ 20 ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰ ተገልጿል፡፡

ከተሳፋሪዎቹ መካከል ሼሪል ቦርማን የተባለችው ግለሰብ ለሲኤንኤን ቴሌቪዥን አርብ ዕለት አመሻሽ አካባቢ አውሮፕላኑ በሚያስፈራ ሁኔታ ተንሸራቶ ወንዝ መግባቱን ገልጻለች፡፡

"በውሃ ውስጥ ነበርን፤ ወንዝ ወይም ውቅያኖስ እንደሆንን በወቅቱ መንገር አልቻልንም" በማለትም የነበረውን ክስተት አስረድታለች፡፡

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)