በሩሲያ ባጋጠመ የአውሮፕላን አደጋ የ41 የሰዎች ህይወት አለፈ

በሩሲያ ርዕሰ ከተማ ሞስኮ ባጋጠመ የአውሮፕላን አደጋ የ41 የሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

ንብረትነቱ የኤሮፍሎት የሆነው አውሮፕላን 73 ተሳፋሪዎችን እና አምስት የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ከሞስኮ ወደ ሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል ሙሩማንስክ ከተማ ለማረፍ በማኮብኮብ ላይ እያለ አደጋው ማጋጠሙ ተገልጿል፡፡

በአደጋው በአውሮፕላኑ የነበሩ የ41 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ሁለቱ ህጻናት ናቸው ተብሏል፡፡  

የተቀሩት 37 መንገደኞች በአውሮፕላኑ የአደጋ ጊዜ መውጫ በመጠቀም ከአደጋው በህይወት መትረፍ ችለዋል።

የሩሲያ ባለስልጣናት የአደጋው መንስኤ እስከአሁን እንዳልታወቀና ለማጣራት ምርመራ መጀመሩን ገልጸዋል፤ ነገር ግን አንዳንድ በአውሮፕላኑ የነበሩ ተሳፋሪዎች በወቅቱ የነበረው አደገኛ የአየር ጸባይ ለአደጋው መንስዔ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

(ምንጭ፡-  ሪውተርስ)