246 የኮኬይን ከረጢቶችን የዋጠው ግለሰብ አውሮፕላን ውስጥ ሕይወቱ አለፈ

ከሜክሲኮ ከተማ በተነሳው አውሮፕላን ተሳፋሪ የነበረው ጃፓናዊ 246 ከረጢት ኮኬይን በመዋጡ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

በዚህም ምክንያት በረራው በጃፓኑ ናሪታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍ የሚጠበቅበት ቢሆንም በሜክሲኮዋ ሶኖራ ግዛት ለማረፍ ተገዷል።

ባለስልጣናት እንዳሉት ዩዶ ኤን የተባለው ግለሰብ ሆዱ ውስጥ በደበቀው ዕፅ ምክንያት ጭንቅላቱ ውስጥ ባጋጠመው የፈሳሽ መጠራቀም ሳቢያ ሊሞት ችሏል።

ይህ ግለሰብ ከኮሎምቢያ ዋና ከተማ ቦጎታ የጀመረውን ጉዞ ቀይሮ ወደዚህ በረራ እንደገባም ታውቋል።

የሶኖራ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በሰጠው መግለጫ መሠረት የእፅ ከረጢቶቹ 2.5 ሴንቲ ሜትር ርዝመትና 1 ሴንቲ ሜትር ስፋት አላቸው። በግለሰቡ ላይ በተደረገው የውስጥ አካል ምርመራም እነዚህ ከረጢቶች በግለሰቡ ሆድና አንጀት ውስጥ እንደታዩ ተነግሯል።

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)