ናሳ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ

የአሜሪካዉ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ጎብኚዎች ዓለም አቀፉን የህዋ ጣቢያ እንዲጎበኙ እድል አመቻችቷል፡፡

ናሳ ባወጣው መረጃ ይፋ እንዳደረገው ለአንድ ወር በሚቆየው የጉብኝት ፕሮግራም ለአንድ ቀን 30ሺ ዶላር አልያም 31ሺ ዩሮ መክፈል የሚችል ማንኛዉም ጎብኚ ዓለም አቀፉን የህዋ ጣቢያ መጎብኘት ይቻለዋል።

ናሳ ይህንን ጉብኝት ማዘጋጀቱ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ለጎብኚዎች ዝግ የነበረዉን አሰራር የቀየረና ከቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ገቢን ለማግኘት የሚያስችል ነዉ ተብሏል።

ለጉብኝቱም በቦይንግ የተመረቱ የበረራ መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይዉላሉ የተባለ ሲሆን፤ በቀጣይ ጊዜያትም ናሳ የ30 ቀናት ቆይታ የሚኖረዉ የግል ጉብኝት በአመት ሁለት ጊዜ በአለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ እንዲደረግ ሁኔታዎችን ያመቻቻልም ተብሏል።

የመጀመሪያዉ ጉዞም በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2020 እንደሚካሄድ ተገምቷል።

ተጓዦች ለምግብ፣ ለመገናኛ አዉታሮችና ለሌሎች አገልግሎቶችም ክፍያ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፤ የጉዞ ሂደቱንም ቦይንግና ስፔስ ኤክስ የተባለ ተቋም የሚያመቻቹ ይሆናል ፡፡/ ዩሮ ኒዉስ /