426 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ መመለስ

መስከረም 6/2014 (ዋልታ) በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን እንዲመለሱ እየተደረገ ባለው ጥረት 426 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ፡፡

በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ 158 ህጻናትን ጨምሮ 426 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።