አሜሪካ ከቻይና የሚገቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

አሜሪካ ወደ ሀገሯ የሚገቡ የፈጠራ ውጤቶችን በተለይም ከቻይና የሚገቡ እና የሰውን ተግባር የሚከውኑ ሮቦቶች እንዲሁም  መሰል የፈጠራ ውጤቶች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ለህግ አስፈፃሚው አካል ትዕዛዝ አስተላልፋለች፡፡

አሜሪካ  ይህን ውሳኔ ስታስተላልፍ የሀገሯን ደህንነት ለመጠበቅ እና በተለይ ቻይና በፈጠራዎቿ ሀገሬን ልትሰልል ዝግጅት አድርጋለች የሚል ጭምጭምታ በመስማቷም እንደሆነ ወሬዎች እየተናፈሱ ነው፡፡

ይህ ውሳኔ ያስደነገጣት ቻይና በበኩሏ የፈጠራ ውጤቶቹ በአሜሪካ ገበያ እየደራላት እና እየተሟሟቀ ባለበት በዚህ ውቅት መሆኑ እጅጉን አሳዝኗታል፡፡

ቻይና ይህ ውግዘት እና ማዕቀብ የተጣለባት ባለፈው  አሜሪካ የሰራቸውን ታንክ ቻይና አሻሽላ መስራቷ እና አሜሪካ የምታመርታቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመቅዳት  ለአለም ሀገራት በማከፋፈሏ እንደሆነም ይነገራል፡፡

አሁን ደግሞ በአሜሪካ የጦር መሳርያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለላ አድርጋብኛለች በሚል ጥርጣሬ የቴክኖሎጂ ምርቶቹ እንዳይገቡ የገቡትም በገበያ ላይ ላልተውሰነ ጊዜ እንዳይሸጡ አግዳለች፡፡

የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የውጭ ንግድ ትስስሩ በደንብ መፈተሸ እና  ከደህንነት ጋር መቃኘት አለብት ይላሉ፡፡

ቻይና ባለፈው አመት ብቻ ከመሰል ፈጠራዎች 45.6 ቢለዬን ዶላር ከአሜሪካ ያገኘች ሲሆን በዚህ ዓመት ደግሞ እስከ አሁን ባለው  ንግድ  22 ቢሊዬን ዶላር አግኝታልች፡፡

ቻይና ቴክኖሎጂዎችን ለአሜሪካ በማቅረብ  ለዘርፉ የምታቀርባቸውን ምርቶች መቶ በመቶ ለማሳደግ እና ትርፉንም  መቶ በመቶ  ለማግኘት አቅዳ እየሰራች ነበር፡፡

 ቻይና ወደ አሜሪካ የተለያዩ በቴክኖሎጂ የመጠቁ የጦር መሳርያዎች  ስማርት ስልኮች፣የልጆች መጫወቻ፣ የስለላ  ካሜራዎች የሰውን ተግባር ተክተው መስራት የሚችሉ የሰው ልጅ አምሳያ ሮቦቶች እና መስል ፈጠራዎችን ትልካለች፡፡

በአሜሪካ በኩል እገዳውን በቻይና ላይ ከመጣል ባለፈ እገዳው እሰከመቼ እንደሚቆይ ያለቸው ነገር የለም፡፡