ግብጽና ጀርመን በተለያዩ ዘርፎች ስምምነት አደረጉ

ግብፅና ጀርመን ለታዳሽ ኃይል፣ ለትምህርት ማስፋፊያና ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበቻ የሚውል የ 203.5 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈራርመዋል ።

የግብፁ ፕሬዚደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጀርመን በጉብኝት ማድረጋቸው ተከትሎ ግብፅ የኢንቨስትመንት ሚኒስትሩ ሳሃር ናስር እና የጀርመን የልማትና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ገርድ ሙለር ጋር ሶስት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈረሙት ስምምነቶች የታዳሽ ሃይል፣ የትምህርት፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን አቅም ለማጎልበት ሲሆን ለዚህም 203.5 ሚሊዮን ዩሮ በጀት ተመድቦለታል ነው የተባለው፡፡ 

ግብፅ የኢንቨስትመንት ሚኒስትሯ ናስር እንደተናገሩት በሁለቱ ሃገራት በተደረገው የልማትና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት መሰረት ለቴክኒክና ሞያ ትምህርት የስልጠናና ማሻሻያ ፕሮግራምና ለፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሚውል 50 ሚሊዮን ዩሮ ተመድቧል፡፡

ሌላው ስምምነት ደግሞ የተለያዩ የልማት ዘርፎችን ለመደገፍ 12 ሚሊዮን ዩሮም ተመድቧል፡፡

በፋይናንስ ትብብር ማዕቀፍ ውስጥ 141.5 ሚሊዮን ዩሮ  ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል የተባሉ ፕሮጀክቶች ይውላል ነው የተባለው፡፡

ይህ በሁለቱ ሃገራት የተፈረመውና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል የተባሉ  ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት፣ የታዳሽ ሃይል፣ የሃይል ውጤታማነት ፣ የንፅህናና የደረቅ ቆሻሻ ፣ የውሃ ሃብት ልማት ናቸው፡፡

ይህ ደግሞ በሁለቱ ሃገራት ያለው የፖለቲካዊና የኢኮኖሚያዊ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ከማጠናከሩ ባለፈ ጀርመን ከትልልቅ የአውሮፓ ለጋሽ ሃገራት መካከል አንዷ እንድትሆን የሚያደርጋት  ነው ፡፡ ሲሉ ግብፅ የኢንቨስትመንት ሚኒስትሯ ናስር ገልፀዋል፡፡

ጀርመን የኢንቨስትመንት አቅሟን ከፍ በማድረግ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ በአሁኑ ወቅትም 1039 የጀርመን ኩባንያዎች በግብፅ ይገኛሉ ፡፡