ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር ሁሉም የነዳጅ ምርቶች 

የንግድ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ ከተማ በነሐሴ ወር ከነበረው የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በ83 ሳንቲም ጭማሪ ተደርገበታል።

በዚህም ባለፈው ወር የነበረው የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ 14 ብር ከ97 ሳንቲም በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም በ15 ብር ከ80 ሳንቲም የሚሸጥ ይሆናል።

የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ግን በነሐሴ ወር በነበረው የሽያጭ ዋጋ እንዲቀጥሉ ተወስኗል።

ውሳኔው በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን ዋጋ መነሻ ተደርጎ እንደአስፈላጊነቱ ሊስተካከል አንደሚችልም ገልጿል።

የነዳጅ ምረቶች የችርቻሮ ዋጋ የተወሰነው የሚኒስትሮች ምክርቤት በመስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ነው ።