አየር መንገዱ ወደ ሶስት አዳድስ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች በረራ መጀመሩን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶስት አዳዲስ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች በይፋ በረራዎችን   እንደጀመረ አስታውቋል።

አየር መንገዱ በይፋ በረራ የጀመረባቸው መዳረሻዎች ኪሳንጋኒ፣ መቡጂማይ እና ኖሰይቢ መሆናቸውም ነው የተገለፀው ።

አየር መንገዱ በረራ ከጀመረባቸው ከተሞች ውስጥ ሁለቱ ማለትም ኪሳንጋኒ እና መቡጂማይ በዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ የቲሾፖ እና ካሳይ ኦሪዬንታል  ግዛቶች እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ሌላኛዋ ከተማ  ደግሞ በሰሜን ምእራብ ማዳካስካር የምትገኝ ደሴት ናት።

አየር መንገዱ ይፋ ያደረጋቸው አዳዲስ መዳረሻዎች በሶስት ወራት 9 አዳዲስ አለም አቀፍ መዳረሻዎች እንዲኖሩት የያዘው እቅድ አካል መሆናቸውን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን ተናግረዋል።

በአፍሪካ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የገዘፈ ስም ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስካይትራክስ ዓለም ዓቀፍ አየር መንገድ ባለ አራት ኮከብ ምስክር ወረቀት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል። (አየር መንገድ ድረ ገጽ)