ኢትዮጵያና ማልታ ያለተጨማሪ ቀረጥ ምርቶችን ለማስገባት ተስማሙ

ማልታ ቫሌታ ከተማ ላይ በተካሄደው የቢዝነስ ሴሚናር ኢትዮጵያና ማልታ ያለተጨማሪ ቀረጥ ምርቶችን ለማስገባት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሴሚናሩ ኢትዮጵያ ለማልታ ባለሃብቶች ምቹ መሆኗን ለማስገንዘብ የተዘጋጀ ነው፣

በኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አክሊሉ ኃይለሚካኤል የተመራ የልዑካን ቡድን በሴሚናሩ ተሳትፏል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት እድሎች፣ ደንቦችና ሊያስገኙ በሚችሉ ጥቅሞች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዶክተር አክሊሉ የተመራው ቡድን ታላላቅ የግብርና እና የምግብ ማቀነባበሪያ ኩባንያዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎችን መጎብኝታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያደረሰን መረጃ አመላቷል፡