ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሀገራቸው በሚገቡ የብረትና አሉምኒየም ምርቶች የወሰኑት ቀረጥን ለ30 ቀናት አራዘሙ

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሀገራቸው በሚገቡ የብረት እና አሉምኒየም ምርቶች የወሰኑት ቀረጥን ለ30 ቀናት አራዘሙ፡፡

ይህም ካናዳ፤የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እና ሜክሲኮ ወደ አሜሪካ በሚልኩት ብረት እና አሉምንየም ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ የሚያደርግ ነው፡፡

ባሳለፍነው ወርሀ መጋቢት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሀገራቸው በሚገቡ የብረት ምርቶች 25 በመቶ እንዲሁም በአሉምንየም አስር በመቶ ቀረጥ መጣላቸው ይታወሳል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ለተወሰኑ ሀገራት በጊዝያዊነት ከወሰኑት ቀረጥ ነጻ የሚያደርግ ዉሳኔ ያካተቱ ሲሆን፤ካናዳ፤የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እና ሜክሲኮ ፕሬዝዳንቱ ከወሰኑት ቀረጥ በጊዝያነት ነጻ እንዲሆኑ ይደነግጋል፡፡

ታድያ ፕሬዝዳንቱ ይህን ዉሳንያቸው ለ30 ቀናት ማራዘማቸው ነው ያስታወቁት፡፡

የንግድ ባላንጣው ቻይና በስምምነቱ ያልተካተተች ስትሆን ከአሜሪካ በምታስገባቸው ምርቶች ላይ የራሷን ቀረጥ ጥላለች፡፡

ይህን ተከትሎም ፕሬዝደንቱ በሀገራቸው እና በቻይና በተፈጠረው እሰጣ ገባ የሚያባብስ ብለውታል፡፡

ደቡብ ኮርያ ወደ አሜሪካ በምትልከው 30 በመቶ ብረት እስካሁን ግልጽ የቀረጥ መጠን ውሳንያቸው ያላሳወቁት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከተለያዩ ሀገራት በተናጠል የሚያደርጉት የቀረጥ ስምምነት በአለም አቀፍ ንግድ ተጽእኖ ይፈጥራል የሚል ስጋት እንዳለ ዘገባው አመላክቷል፡፡

የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዱ በሀገራቸው የተወሰነ ውሳኔ መሰረት በማድረግ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር ተከታታይ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ካናዳ ወደ አሜሪካ ብረት በብዛት ከሚልኩ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ስሆን የፕሬዝዳንቱ ዉሳኔ ማራዘም በሚመለከት ግን ስለጉዳዩ ከፕሬዝደንቱ ጋር እንደሚወያዩ ነው ያስታወቁት፡፡

የፕሬዝዳንቱ የቀረጥ ዉሳኔዎች በአለምአቀፉ ንግድ ያላቸው ተጽእኖ እያጠና እንደሆነ የገለጸው የአውሮፓ ህብረት ዉሳኔዎቹ ሁሉም ሀገራት እኩል ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆን እንዳለባቸው ነው ያስታወቀው፡፡

የሰሜን አሜሪካ ነጻ የንግድ ስምምነት (NAFTA)አባል ሀገራት ባደረጉት ዉይይት ካናዳ እና ሜክሲኮ እስከ ግንቦት አንድ ባለው ግዜ ከቀረጥ ነጻ የሚያደርጋቸው ስምምነት መድረሳቸው ያወሳው መረጃው በሚቀጥለው ሳምንትም ዉይይቱ እንደሚቀጥል አመላክቷል፡፡ (ቢቢሲ)