ተመራማሪዎች አስምን ለማከም የተሻለ መንገድ እግኝተናል ብለዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19/2008 (ዋኢማ)-የመተንፈሻ አካል እክል የሆነው አስም በዓለማችን ላይ በርካታ ሰዎችን እንደሚያጠቃ ይነገራል።

በቅርቡ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው በዓለማችን ላይ ከ300 ሚሊየን በላይ ሰዎች የአስም ችግር እንዳለባቸው ያሳያል።

ይህንን ችግር መለቅረፍም የተለያዩ ህክምናዎች የሚደረጉ ሲሆን፥ የህመሙ ተጠቂዎች የመተንፈሻ አካላቸው በመቆጣት የመተንፈስ ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜ ይህንን ለማስቆም የሚያግዝ ህክምና ነበር የሚሰጠው።

ይህ ህክምና ግን ጊዜያዊ መፍትሄ የሚሰጥ እንጂ ህመሙን ለማስቆም እንደማይረዳ ነው የሚነገረው።

ተመራማሪዎች በቅርቡ ባደረጉት ጥናት ግን የመተንፈሻ አካል ህመም የሆነውን አስምን ለማከም ከዚህ በፊት ከነበረው ህክምና የተሻለ መፍትሄ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

በእንግሊዝ የሳውዝሀምፕተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በዘረመል (Gene) ላይ በሚደረግ ህክምና አስምን ማዳን እንደቻሉ ነው የሚናገሩት።

ህክምናው “ADAM33” በሚባል ዘረ መል ላይ የሚካሄድ መሆኑንም አስታውቀዋል።

“ADAM33” የሚባለው ዘረ መል ኢንዛይም የሚያመነጭ ሲሆን፥ አየር በሚወጣበት እና በሚገባበት የሰውነት ክፍል አካባቢ የሚገኝ ነው።

ኢንዛይሙ ከተጣበቀበት ስፍራ ላይ በሚለቅበት ጊዜ ወደ ሳንባችን አካባቢ የሚገባ ሲሆን፥ የመተንፈሻ አካላችን አካባቢ ላይ መጨናነቅን በመፍጠር የአተነፋፈስ ችግር ያስከትላል ተብሏል።

በሳውዝ ሀምፕተን ዩኒቨርሲቲ የመተንፈሻ አካላት ላይ ምርምር ያደረጉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሚካኤል ሃትቺ፥ ይህንን ዘረ መል ስራ በማስቆም አስምን ማከም ችለናል ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ ግኝታቸው በሙከራ ደረጃ ውጤታማ መሆኑን የሚናገሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሚካኤል ሃትቺ፥ በቀጣይም በስፋት ውጤታማ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)