በቂ ውሃ አለመጠጣት ከልክ ላለፈ ውፍረት ይዳርጋል-ጥናት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23/2008(ዋኢማ)-ውሃን አዘውትሮ መጠጣት ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይታወቃል።

ለዚህም ሲባል አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በርካታ መጠን ያለው ውሃ በቀን ውስጥ እንዲጠጡ ይመከራል።

አንድ ሰው በቀን በአማካኝ ከስድት እስክ ስምንት ብርጭቆ ውሃ ቢጠጣ መልካም ነው የሚለውንም በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ከሰሞኑ አዲስ የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ደግሞ በቀን ውስጥ ለአንድ ሰው የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን የማይጠጡ ሰዎች ከልክ ላለፈ ውፍረት የመጋለጥ እንድላቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

“አናልስ ኦፍ ፋምሊ ሜዲስን” በሚል መፅሄት ላይ የታተመው ይህ መረጃ በቀን ውስጥ በቂ ውሃ የማይጠጡ ሰዎች በቂ ውሃ ከሚጠጡት ጋር ሲነጻጸሩ በ1 ነጥብ 5 እጅ ከልክ ላለፈ ውስፍረት የመጋለጥ እድል አላቸው ይላል።

ተመራማሪዎቹ አንድ ሰው የሰውነት ክብደቱን መቆጣጠጣር ከፈለገ ውሃን ከግምት ውስጥ ማስገባት የግድ ነው ሲሉም አስፍረዋል።

በጥናቱ መሰረትም አንድ ሰው ቀን ውስጥ ከ6 እስከ 8 ብርጭቆ ፈሳሽ መውሰድ አለበት የተባለ ሲሆን፥ ፈሳሹ ከውሃ በተጨማሪ የስብ መጠኑ አነስተኛ የሆነ እና ስኳር ያልበዛበት ወተት መጠጣትም ይቻላል ብለዋል።

ጥናቱ በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ ሲሆን፥ በጥናቱ ላይ እድሜያቸው ከ18 እስከ 64 የሆኑ 9 ሺህ 500 ሰዎች ተካፋይ ሆነዋል።

በዚህም የእያንዳንዱን ሰው የቦዲ ማስ አንዴክስ የመረመሩ ሲሆን፥ በዚህም ምን ያክል የውሃ መጠን ሽንታቸው ውስጥ ይገኛል የሚለውን ለክተዋል።

በጥናቱ መሰረትም በቂ ወሃ የማይጠጡ ሰዎች ከሚጠጡት ይልቅ ቦዲ ማስ ኢንዴክሳቸው ከፍተኛ ሆኖ መገኘቱን መለየት እንደቻሉ ነው ተመራማሪዎቹ ያስተወቁት።

በቂ ውሃ የማይጠጡ ሰዎች በ1 ነጥብ 5 እጅ ከልክ ላለፈ ውስፍረት የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ መሆኑምን አረጋግጠናል ብለዋል ተመራማሪዎቹ።

ውሃ ለሰው ልጅ በጣም ጠቃሚ ነው የሚሉት ተመራማሪዎቹ፥ በተለይም የሰውነታቸውን ክብደት መቆጣጠር የሚፈልጉ ሰዎች ውሃን በአግባቡ መጠጣት አለባቸው የሚል ምክርም አክለዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)