ከ17 በላይ የበሽታ አይነቶችን መለየት የሚያስችል መሣሪያ ተሠራ

ተመራማሪዎች በትንፋሽ በመጠቀም ብቻ ከ17 በላይ የበሽታ አይነቶችን መለየት የሚያስችል መሳሪያ  መሠራታቸውን ገለጹ ፡፡  

በአለማችን በየቀኑ በተለያየ አይነት በሽታዎች ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ ለዚህም ተመራማሪዎች በሽታን የሚከላከሉ አልያም በሽታዉን በቀላሉ ሊፈዉሱ የሚችሉ መድሃኒቶችን ያመርታሉ፡፡

በየግዜዉ የሚሰሩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ህይወትን ለማቅለል ወሳን ድርሻ እንዳላቸዉ ይታመናል፡፡

 ደይለሊ ሜይል በዘገባዉ ያወጣዉ መረጃም ይህን ሃሳብ የሚያጠናክር መረጃ ነዉ፡፡አሁን ግን ይህንን ስጋት የሚቀንስ እና በቀላሉ  በአፍ በሚወሰድ ትንፋሽ  በቀላሉ በምን አይነት በሽታ እንደተጠቀቁ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል ሲሉ እስራኤላዉያን ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡

በተለይ ቀደም ባሉት አመታት  ሰዎች የህመማቸዉ መንስኤ ባለማወቅ ሚሊየኖች ህይወት ጠፍቷል፡፡በቀጣይም አዲሱ ግኝት ምናልባም ሰዎች በበሽታዉ ተጠቅተዉ ለሞት ከመድረሳቸዉና በህመም ተጠቅተዉ መጨረሻ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸዉ በፊት ፈጥነዉ መፈወስ እንዲችሉ ይህ መሳሪያ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ሲሉተመራማሪዎቹ አብራርተዋል፡፡

ቀደም ባሉት አመታት በተለያየ ምክንያት የሚከሰተዉ በሽታን ለመቀነስ እና ቀድሞ በማወቅ ለመቀነስ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ታድያ አሁን ተገኘ የተባለዉ አዲሱ በትንፋሽ ህመምን ለመለየት የሚያስችል መሳሪያ መፍተራቸዉ እፎታይን የሰጥቷል ይላል ከደይሊ ሜይል የተገኘዉ መረጃ፡፡

የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የተሰራዉ የቴክኖሎጂ ዉጤት አሽከርካሪዉ በደሙ ዉስጥ ምን ያህል የአልኮል መጠን መዉሰዱን እንደሚያሳዉቀዉ ሁሉ ይህ አዲሱ የትንፋሽ መሳሪያም አፍ ዉስጥ በሚሰጠዉ ትንፋሽ ከ17 በላይ የህመም አይነቶችን መለየት ያስችላም ተብሏል፡፡

ሰዎችበምን አይነት ህመም መጠቃታቸዉን ለማወቅ እስከአሁን የተለመደ በደም አማካኝነት የሚደረገዉን ምርመራ ሲሆን አዲሱ መሳሪያ ግን ከዚሀም በላይ የተሸለ ዉጤት በመስጠት የበሽታዉን አይነት በትክክል ይለያል ነዉ የተባለዉ፡፡

ይህ አዲሱ መሳሪያ ና ኖዝ የተሰኘ ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ አርቲፊሻል አፍንጫ እንደ ማለት ነዉ፡፡

አሜሪካዉያን የምርምር ቡድን መሳሪያዉን በአፍሪከሳዊቷ ሃገር ማላዊ በወባ በሽታን ለመለየት ባደረጉት ሙከራም መሳሪያዉ የእያንዳንዱን የተለየ ተንፋሽ እንደ እድሜዉ ፆታ እና ዘር ለይቶ ማሳየት ዉጤታማ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

 ምናልባትም ሰዎች ህመማቸዉን ለማወቅ የሚያወጡትን ወጪ የሚቀንስና ምናልትም በምርመራ ሂደትን ህመም አልባ እና ቀላል ያደርገዋል ተብሏል፡፡

የእስራኤል የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የምርምር ቡድን እደገለፁት ና ኖዝ የተሰኘዉ አዲሱ መሳሪያ ከሌሎች ህመሞችን ከማሳወቅ በተጨማሪ የካንሰር አይነቶችን መለየት የሚችል ሲሆን ይህም 86 በመቶ የሚሰጠዉ መረጃ ትክክለኛ እንደሆነ ነዉ አረጋግጠዋል፡፡