በኡጋንዳ በተከሰተ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

በቫይረሱ ምክንያት በኡጋንዳና ኬኒያ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን የአለም ጤና ድርጅት በትላንትናው እለት አስታዉቋል ። 

አለም አቀፉ የጤና ድርጅት የማርበርግ ቫይረስ ከኢቦላ ቫይረስ ጋር ተዛማጅነት መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ ሁለቱ ቫይረሶች የ ፍላፈረስ ምድብ አይነት ሲሆኑ የሥርጭት መጠናቸው ከፍተኛ ነዉ ተብሏል፡፡ በማርበርግ ቫይረስ አማካይነት የሚከሰተዉ በሽታ 88 በመቶ ለሞት ሊዳርግ መቻሉ ደግሞ ክስተቱን አሳሳቢ ነዉ ሲል ተቋሙ ያስቀምጣል፡፡

እንደ ኢቦላ ቫይረስ ሁሉ የማርበርግ ቫይረስ ከባድ የጤና ችግር የሚያስከትል ሲሆን ይህም የሰውነት  ትኩሳት እና የሰውነት ደም ቧንቧ ዝውውር መዛባት የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ ይባሱኑ ደግሞ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ማስከተሉ ለቁጥጥር ከባድ እንደሚያደርገውም ተመላክቷል፡፡
የቫይረሱ ምልክት መታየት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከአምስት እስከ ሰባት ባሉት ቀናት ውስጥ እንደሚከሰት ነዉ የአለም ጤና ድርጅት ያስታወቀዉ፡፡ ደም የተቀላቀለበት ማስመለስና ሰገራ የሚከሰት ሲሆን ከታማሚዉ አፍንጫና ሰዉነት ከፍተኛ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም ይችላልም ተብሏል፡፡ 

ቫይረሱ በነርቭ ላይ ጉዳት ከማድረሱም በተጨማሪ ግራ መጋባት እና አልፎ አልፎም ያልተለመደ ንዴት ሊያስከትል  እንደሚችል ተቋሙ ጨምሮ አስታዉቋል፡፡ቫይረሱ ከተከሰተ በስምንትና ዘጠኝ ቀናት ዉስጥ በሚፈጠረዉ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ለህልፈት ሊዳርግ ይችላል ነዉ የተባለዉ፡፡

ወረርሽኙ ከተከሰተ 18 ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን በቫይረሱ ምክኒያት ሶስት ሰወች  በምስራቅ ኡጋንዳዋ ኪዊን ከአንድ ቤተሰብ መሞታቸዉ ታዉቋል፡፡

ኡጋንዳ ቫይረሱን ከሁት አመት በፊት በቁጥጥር ስር ማዋሏን ያስታወሰዉ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት አሁን ላይ  ሰርጭጽ 100 ደርሷል ሲል የዘገበዉ ኒዉስ ናዉ ነዉ፡፡ ( ምንጭ:ዳይሊ ማል)