በኤች አይ ቪ ኤደስ የተያዙ ዜጎች በአባላዘር በሽታ የመያዝ እድላቸው 20 በመቶ እጥፍ ነው

በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በአባላዘር በሽታ መያዛቸውን በጥናት ተረጋግጦል።

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የበሽታ መከላከል ዳይሬክተር አማካሪ ዶክተር ካሳሁን አሸብር ለዋልታ እንደገለጹት ከነዚህም ውስጥ የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የአባላዘር በሽታ የመተላለፊያ መንገዱ አንዱም ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት መሆኑን የገለጹት አማካሪው የአባለዘር በሽታ የምንላቸው ከ30 አይነት በላይ ቫይረሶችና ባክቴሪያዎች ሲሆኑ በተለይ  አምስቱ በኢትዮጵያ ይገኛሉ ብለዋል።

እነሱም ጨብጥ፣ ከርክር፣ ቂጢኝ፣ ባቡሌና ኤችአይቪ ኤድስ ናቸው።

በአባላዘር በሽታ የተያዘ ሰው የተለያየ ምልክቶች የሚያሳይ ሲሆን በወንዶችም በሴቶችም የመራቢያ አካላት ላይ የተለያዩ ለውጦችን የሚያስከትል ሲሆን እብጠት ቁስለት እንዲሁም ሽታ ያለው ፈሳሽ ነገሮች እንዳላቸው ዶክተሩ ካሳ ነግረውናል።

ለሁሉም የአባላዘር በሽታ መነሻ ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነትና የደም ንክኪ  ቫይረሱ በቀላሉ ከሰው ወደሰው እንዲተላለፍ ያደርጋል።

በቫይረሱ የተያዘች ነፍሰጡር እናት በክትትል  ተገቢውን ህክምና ካላደረገች ወደፅንሱ በቀላሉ ስለሚተላለፍ ህፃኑ የአካለ ጉዳት ሊያጋጥመው ይችላል።

የአባላዘር በሽታ ለመከላከል በአሜሪካ በየአመቱ ከ16 ቢሊዮን በላይ ለተለያዩ የህከምና ወጪዎች ይውላል ።

በሀገራችንም የጤና  ጥበቃ ሚኒስቴር የአባላዘር በሽታ ለመከላለል  የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

የበሽታውን ስርጭት ለመግታትና ተጎጂዎችን ለማከም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች ህክምናው ያለምንም ክፍያ በሁሉም የመንግስት ተቋማት እንዲሰጥ በማድረግና የአሰልጣኖች ስልጠና በመስጠትና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፈጠር የመከለከል ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። 

በኤች አይ ቪ ኤደስ የተያዙ ዜጎች በአባላዘር በሽታ የመያዝ እድላቸው 20 በመቶ እጥፍ ነው ተባለ።