ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን የሆነውን የባቡር መሥመር ሙከራ በተሳካ ሁኔታ አካሄደች

ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን የተባለውን አዲስ የባቡር መሥመሯን ሙከራ በተሳካ ሁኔታ  ማካሄዷን  አስታወቀች ።

ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን እና ዘመናዊ የተባለለትን ባቡር ወደ ሥራ ለማሰገባት  በተያዘው አመት የተለያዩ ሙከራዎችንም ሰታደርግ ቆይታለች፡፡

ይህ አዲስ የባቡር መስመር ከፈረንሳይ በተገኝ 2 ቢሊየን ብድር  በፈረንሳዩ የልማት ድርጅት እና  በሞሮኮው ብሄራዊ የባቡር ድርጅት በተደረገው ስምምነት አማካኝነት ሲገነባ ቆይቷል፡፡

የሀገሪቱ የባቡር ድርጅት ባሳለፈነው ሀሙስ የተሳካ ሙከራ ማድረጉንም ይፋ አድርጓል፡፡

ሙከራው የመጨረሻ ነው የተባለ ሲሆን ከዚህ በኋላ ወደ ሥራ ለመግባት ብቃት እንዳለውም ነው የተገለፀው፡፡

በሙከራው ወቅት በሰዓት 320 ኪሎ ሚትር የተጓዘ ሲሆን ይህም እጅግ በጣም ፈጣኑ ነው ተብሎለታል፡፡ የሀገሪቱ የባቡር ድርጅት ኦኤንሲኤፍ በሰጠው መግለጫ ይህ ሳምንት ለሀገሪቱ ታሪካዊ እና አሰደሳች ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ይህ ዘመናዊና ቴክኖሎጂ ለበስ ባቡር ሀገሪቷን ከአፍሪካ ቀዳሚ ከማድረግም ባሻገር በተለያየ ዘርፍ ለምታደርገው እንቅስቃሴ ሚናው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

ለተሳፋሪዎቹ ቀልጣፋ ምቹ እና በውስጡም የተለያዩ አገልግሎቶቹን በቀላሉ ማቅረብ  የሚያሰችላቸው ይህ አዲስ ባቡር እኤአ በ2018 የካቲት ወር ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ይገባል ተብሏል፡፡(ምንጭ: ከዘቴሌግራፍ)